Tuesday, December 29, 2015

በአገራችን ኢትዮጵያ ድርቅ ባጠቃቸው ኣከባቢዎች በረሃብና በችግር የሚጠቁ ወገኖቻችን ለማዳን፣ መንግስት የሚገባ እርዳታ በማደል ላይ ኣለመሆኑን ተገለፀ።



    በመረጃው  መስረት  ድርቅ ባጠቃቸው  አከባቢዎች የሚኖሩ ወገኖቻችን በገዥው የኢህዴግ ስርአት የሚፈለገዉን ድጋፍ ስላልተደረገላቸው በድርቅና በችግር የሚሰቃዩ ዜጎቻችን ብዙ መሆናቸውና፣ ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የሚገኝ እህልም የተረጂው ቁጥር ስለበዛ ሊዳረስ ባለመቻሉ ምክንያት  እርዳታው በእጣ እየተከፋፍለ መሆኑን የአይን ምስክሮች መሰረት በማድረግ መረጃው አስረድቷል።
      መረጃው ኣስከትሎ እንዳስረዳው የዜጎቻችን  ህይወት በረሃብና በሽግር  በመሰቃየት ላይ እያሉ፣ አስተዳድሪዎቹ ግን ለእርዳታ ተብሎ  የመጣው  እህል በማከፋፈል ላይ አድልዎ እየፈፀሙ በመሆናቸው የተነሳ፣ ረሃብ የወለደው  አደጋ  እየተባባሰ መሆኑንና ገዥው ስርአትም ድርቅ ያጠቃቸው ኣከባቢዎች  በትኩረት   ኣይቶ ሊንቀሳቀስ ካልቻለ፣ በአደጋ የሚጠፋ ህይወት ሊባባስ  እንደሚችል  የአይን መረጃዎች ኣስገንዝበዋል።