በመረጃው መሰረት፣ በትግራይ ክልል ሰ/ምእራብ ዞን ፀለምቲ ወረዳ ውህደት ቀበሌ በወንጀል መከላከል በሚል ስራ ተሰማርተው የሚገኙ ፖሊሶች የተሰጣቸውን ህዝባዊ
ሃላፍነት ወደጎን በመተው፣ የህዝብን ገንዘብ በመዝረፍ ላይ ከተሰማሩ
ሌቦች ጋር በመመሳጠር በሚፈፀመው የወንጀል ተግባር እጃቸው በማስገባት በህዝቡ ላይ ተጨማሪ ችግር በመፍጠር ላይ መሆናቸወን ተገለፀ።
መረጃው ጨምሮ፣ እነዚህ ያልደከሙበትን የህዝብ ገንዘብ በመዝረፍ ላይ የተሰማሩ
ሰዎችን ፖሊሶች በቁጥጥር ሰር እንዲያውልሏቸውና፣ የአከባቢው ነዋሪዎችም ተባብረው በመያዝ ወደ ሕግ ቢያቀርቧቸውም እንኳ እነዚህ የሕግ ተጣባቂዎች ነን የሚሉ ፖሊስ ደግሞ የራሳቸወን ወንጀል እንዳይታወቅ በማሰብ፣ ለሌቦቹ ከህግ ውጭ ፈትተው እንደሚለቋዋቸውና
ሌቦቹ ተመልሰው ላስያዝዋቸው ነዋሪዎች ጉዳት በማደረስ ላይ መሆናቸው ታውቋል።