Tuesday, January 5, 2016

በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን የህዝብ ተቃውሞ ለመጨፍለቅ የተሰማሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት በክልሉ ፕሬዝዳንት ሙክታር ከድር ሙገሳ ተቻራቸው።



መረጃ እንዳስረዳው፣ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙክታር ከድር የአዲስ አበባ ልዩ ዞንና አዲስ አበባ ከተማ ዞርያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ያወጣ አዋጅ ተከትሎ የተከሰተው ድንገተኛ የህዝብ ተቃውሞ፣ በንፁኃንና በፌደራል ፖሊሶች የተወሰደው እርምጃ ከ100 በላይ ገድለው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ በከባድ አቁስለውና አፍነው በመውሰድ በፈፀሙት ድርጊት በክልሉን ፕሬዝዳንት የስራ ሙገሳና መስጋና እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።

   መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው፣ በመስጋናው መድረክ የተገኙት አቶ ሙክታር ከደር፣ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ለመበተን የተሰማሩት የፌደራል ፖሊሶችና ወታደሮች በህዝቡ ላይ በወሰዱት እርምጃና አፍፃፀም ለህዝብ ደህንነት የቆሙ እንደሆኑ የሚያስመሰክር ነው በማለት፣ በጋጠመው የፀጥታ አጠባበቅ ደግሞ በራሱና በኦሮሚያ ክልል መስተዳድሩ ስም ከፍተኛ ምስጋና ለማቅረብ እወዷለሁ ሲል በንፁኃን ዜጎች ላይ የደረሰው የመግደል፤ የመቁሰል፤ የማሰርና የማንገላታት በአጠቃላይ ባወረዱት ጊዜ ይቅር የማይለው ታሪክ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙክታር ከድር እንደ አወንታዊ ተግባር ወስዶ ለፈፀሙት የፀጥታ አካላት ምስጋናና ሙገሳ ማቅረቡ ህዝቡን በይበልጥ እንዳስቆጣው ለማወቅ ተችሏል።