ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው ገዥው የኢህአዴግ
ስርአት የአዲስ ኣበባ ከተማንና በአዲስ አበባ ዙርያ ከሚገኙ የኦሮሞ ከተሞችን በልማት ለመተሳሰር በሚል ፈሊጥ አዲስ የማስተር
ፕላን ኣዋጅ በማውጣታቸው ምክንያት በተለያዩ የኦሮምያ ገጠሮችና ከተሞች የሚገኙ
ነዋሪዎች ለአዲሱ አዋጅ በመቃወማቸው የሰጋው ስርአት በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂ ሃይሎች በማሰማራት በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ ኢ-ሰባዊ የሆነ
ደብደባ በማውረድ ለተማሪዎች ሞትና ቁስለኛ ሲያደርጉት የተቀረዎም
ወደ እስር ቤት በማሰገባት ህዝብዊ ተቃሞውን በሃይል ለማብረድ የሙከራ
እንቅስቃሴ ጌና ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ታወቀ።
በዘህ መሰረትም በታህሳስ 21/ 2008 ዓ/ም የሃርምያ የዩነቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞቻቸውን በስለማዊ መንገድ እየገለፁ በነበሩበት ጊዜ የፈደራል ፖሊስ ኣባላት ወደ
ቅጢር ግቢው በመግባት በወሰዱት የሓይል እርምጃ ሰሶት ተማሪዎች ለግዜው ሲገድሉ ሌሎችም ከአደጋው ለማምለጥ ሲሉ በግድግዳው ዘልለው ለመውረድ በሚሞክሩበት ጊዜ በከባድ እንደተጎዱና 40 የሚሆኑ
ተማሪዎች ደግሞ በፈደራል ፖሊስ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታወቀ፣
መርጃው ጨምሮ እንዳመለከተው በሃረምያ
ዩኒቨስርቲ ተማሪዎች የተነሳው ተቃውሞ በዩኒቨርስቲው ዙርያ
ያለመረጋገትና ግርግር እንደተፈጠረ አሳወቀ።