Friday, January 8, 2016

የአምቦና የነቀምት ከተማ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ከተማና በዙርያዋ በኦሮምያ ዞኖች አስመልክቶ የወጣው አዲስ የማስተር ፕላን አዋጅ አስመልክቶ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ገዥው ስርአት እየወሰደው ያለው የሃይል እርምጃ ሳያግዳቸው እየቀጠሉ መሆናቸውን ታወቀ።



      የተገኘው መረጃ ጨምሮ እንዳመለከተው በአምቦ ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች በታህሳስ 22 ቀን 2008 ዓ/ም ሰልፊ በመውጣት ተቃውሞቻቸውን በሚያካሂዱበት ግዜ፣ የፈደራል ፖሊስ አባላት መንገዶችን ለመዝጋዝት ቢሞኩሩም  ከላይኛው እሰከ ታችኛው ትምህርትቤቶች   የሚገኙ ተማሪዎች  በህብረትና   በታልቅ ወኔ ወደ ሰልፉ መቀላቀላቸው ታወቀ።

   መረጃው በመጨረሻ እንዳስረዳው የህዝብን ተጠቃምነት የሚጎዳ የይስሙላ  ማሰተር ፕላን  የስርአቱ ባለስልጣናት   ህዝቡ ድብደባው ሲበዛበት ተቃውሞውን  ይተወዋል ብለው ቢያስቡም፣ ይህ ጉዳይ መፍትሄ እስካልተደረገለት ድረስ ተቃውሞውን በሆነ ምክንያት ሊቋረጥ እንዳማይችልና እስከ መጨረሻ የህይወት መስዋእትነት እንከፍላለን የሚል ታላቅ ስሜት እንዳላቸው ለማወቅ ተችለዋል።