Saturday, February 20, 2016

የራያ አዘቦ ነዋሪዎች በዚህ አመት ባጋጠመው ከባድ ደርቅ ተከትሎ የተጀመረው እርዳታ በቂ ሳይሆን ለህይውት መሳደርያ ተብሎ ለአንድ ሰው ለወር 15 ኪሎ ሰንዴና ግማሽ ሊትር ዘይት ብቻ እንደሚስጡ ገለጹ።



    የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ እንዲታገዝ የተባለው ህዝብ  ከመሰከረም እሰከ ህዳር ጥቂት ሲሰጥ የቆየ ቢሆኖንም ፥ይህ እየተሰጠው የነበረው አገዛ ተቋርጦ በመቆየቱ ከመጨረሻ  ህዳር ወር ጀምሮ እስከ ለካቲት 5/2008 ዓ/ም ባለመታደሉ በህዝቡ ላይ ከባድ ችግር እየደረሰ እንዳለ ለማውቅ ተችሏል።
  የአሜሪካ ሬደዮ ሰርጭት መረጃ እንዳመለከተው፣ ህዝብ በረሃብ እየተሰቃየ እርዳታው መቋረጡ  የሚያመለከታቸው አካላት  ግልጽ የሆነ መረጃ ለህዝብ  ሳይሰጡና በሜዲያ አዉታሮች እንዳይጋለጥ ተሸፍኖ ለሁለት ወር በመቆየቱ የተነሳ በዚህ ጊዜ  ደግሞ  የተወሰነ እርዳታ  የሚስጡት 15 ኪሎ ሰንዴ ለሁሉም ለተቸገሩ የሚስጥ እንዳልሆነ ከገለጹ ብኋላ፥ በሴፋቲኔት የሚታቀፈው  ከአንድ ቤተሰብ አምሰት የሚል ሆኖ፣ ከአምሰት በላይ ያለው ቤተሰብ እነዚ አምሰቱ ሊሸከሙት እንዳልቻሉ  ነዋሪውቹ መሰረት በማደረግ አስረደተዋል።
    በመጨረሻ የወረዳው አሰተዳዳሪ የሆነው ክፍሎም ሃይለ በበኩሉ ይህ እየተሰጠ ያለው እርዳታ በቂ አይደለም የሚል የህዝብ አስተያየት ትክክለኛ ነው፣ እኛም እናውቃለን ቢሆንም ግን ከላይ በፌዴራል መንግሰት መመሪያ  መሰረት በአገሪትዋ ሙሉ እየተጠቀሙ ያሉት በመሆኑ የሚቀየር አይደለም ብልዋል።
    ይህ ከባድ ድርቅ ባመጣው ምክንያት 18 ሚሊዮን ዜጎዎች  አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጠባቂ ሆነው ባሉበት ወቅት፣ የኢህአዴግ ገዢው ሰርአት  ለእነዚ አስቸኳይ እገዛ የሚጠብቁ ወገኖች በቂ የሆነ ደጋፍ  እያደረግነን ነው የሚሉ እንኳን ቢሆኑም፣ ህዝቡ ግን በተቃራኒው በተለያየ የአገራችን አካባቢ እገዛ አላገኘንም፥ ለዚህም  በእረዳታ ስም ተብሎ የሚመጣ ሰንዴ ገና ወደ ህዝብ ሳይደረስ በመከልከል በሙስና ምክንያት እየጎዱን ናቸው፥ ለህዝብ የሚመጣ እርዳታ በቂ አደለም እያሉ ጥያቄ የሚያሰሙ ቢሆኑም ለጥያቂያቸው አጥጋቢ መፍትሄ  የሚስጥ የመንግስት አካል አላገኘንም  በማለት ምሬታቸውን ገለጸዋል።

No comments:

Post a Comment