Saturday, February 20, 2016

ኢትዮጵያ ከአመታዊ ባጀትዋ 60% የሚሆን ለኮንስትራክሽን ስራዎች ይውላሉ ቢባልም በሙስናና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ስለሚጠፋፉ በስራ ላይ እንደማይውሉ ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት የኢንዳስትሪ ኮንስትራኽሽን በኤኮኖሚ ላይ ያለው ትልቅ ተፃኖ በግምት ላይ በማስገባት ኢትዮጵያ ከ አመታዊ ባጀትዋ 60% የሚሆነው በኮንስትራኽሽን ስራዎች እንዲውል መበጀትዋ ባይከፋም፣ ሆኖም ግን  የተለያዩ ክፍተቶችና ተደጋጋሚ  ጥያቄዎችን ሲነሱ መቆየታቸውና በተለይ ደግሞ ይህ ድርጅት ለሙስና ተጋልጦ በክፍተኛ አደጋ ላይ መቆየቱ የኮንስትራክሽኑ ቴክኖሎጂ ማነጅመንት ማህበር ባለሞያዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት ባካሄዱት ውይይት ላይ ገለፁ።
  ለችግሩ ቁልፍ ምክንያት አድርገው ከጠቀስዋቸው ውስጥ የኢንድስትሪው በዘመናዊነቱና  በሞያ ሰነ-ምግባሩ በአፈፃፀሙ የወረደ ሆኖ መገኝቱ  በድርጅቱ በተለያዩ ክፍሎች ተሳታፊ በመሆን ከሚታወቁት የኮንስታራሽን ኢንድስትሪ ሙሁራኖች ውስጥ  ጥቂቶች መሆናቸው ዶ/ር ኢንጅነር ውብሸት   የባለሞያዎቹ ማህበር ፕረዚዳንት ባቀረቡት ጥናታዊ ሪፖርት አስቀምጠዋል።
   ውይይቱ ካካሄዱት ሙሁራኖች ጨምረው አግባብነተ በሌለው መንገድ በመባከን ላይ ያለው የህዝብ ሃብት ድኖ በአገሪትዋ ልማት እንዲወል ከሆነ፣ ድርጅቱ ከመሪዎቹ ጀምሮ እስከ ተራ ሰራተኞቹ  ብፖለቲካ ሳይሆን ብሞያው የተማሩ ችሎታና አቅም ያላቸው ሊሆኑ ይገባል በማለት ሞያዊ  ምክራቸወን በመሰጠት ውይይቱ እንደተጨረሰ መረጃው በመጨረሻ አገንዝበዋል። 

No comments:

Post a Comment