ባገኘነው መረጃ መሰረት፣ የካቲት 7
/2008 ዓ/ም ከሚዛን ወደ ቴፒ ከተማ ሰዎች ጭና ትጓዝ የነበረችው አውቶቡስ ብቁ የመኪና መንገድ ባለመኖሩ የተነሳ ባጋጠማት የመኪና
መገልበጥ አደጋ፣ ውድያውኑ አንድ ህፃን የሚገኙባቸው 15 ሰዎች ሲሞቱ፣ 32 ሰዎች ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሷቸው ወደ ተፒ
ሆስፒታል እንደተወሰዱ አመልክተዋል።
የሚዛን ቴፒ ዩንቨርሲቲ የሆነችው የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከሚዛን ወደ ቴፒ
ከተማ ተጉዘው የብቃት ማረጋገጫ ( ሲ ኦ ሲ ) ፈተና ወስደው ሲመለሱ የነበሩት የዩንቨርሲቲው ሰራተኞች ጭና በቁ በተባለው ወንዝ
አካባቢ ስትደርስ እንደተገለበጠች መረጃው ያመልክታል።
በመጨረሻ ገዢው የኢህአዴግ ስርአት የመኪና
መንገዶች በአስፋልትና በኮንኩሪት አስፋፍተናል እንዲሁም ትላልቅ ወንዞች በድልድዮች እንዲታነፁ በማድረግ ህዝብ ያለ ምንም ችግር
የተሳለጠ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርገናል በማለት ቀጣይ የሚቀሰቅስበት እንኳ ቢሆን፣ እንደዚህ አይነት ክስተት ግን በየ ቀኑ በተለያዩ
የአገራችን አካባቢዎች፤ ዜጎቻችን እየደረሰ ያለውን የመኪና አደጋ ግን የይድረስ ይድርስ በመሰራታቸው የተነሳ ሳይውሉ ሳያድሩ የተበላሹት
መንገዶች፣ ለአደጋ ተጋልጠው ተገቢውን ጥገና ሳይደረግላቸው ህዝብ እለታዊ ኑሮውን ለማከናወን ከቦታ ወደ ቦታ ሲጓዝ ዋስትና አጥቶ
በየ እለቱ ለሞትና ለካል ጉዳተኝነት ሰለባ እየሆነ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment