በመረጃው መሰረት፣ በኦሮምያ ክልል ምእራብ
አሩሲ ዞን የሚኖር ህዝብ ከገዥው ስርአት ወታሃደሮች ጋር በጥላቻ ተፈጥጦ እንደሚገኝና በተለይ ደግሞ በሻሸመኔና ኣከባቢው የሚገኙ ከተሞች ያለው የህዝብ ቁጣ ለአምስት አመታት ያህል በተከታታይ በገዥው የኢህአዴግ
ስርአት ተቃውሞ በመቀጠል ላይ መሆኑንና፣ አሁንም መንገዶችን በመዝጋትና የገዥው ስርአት ወተሃደሮች መኪናዎችም እንደጋዩ ለማወቅ ተችለዋል።
በአሁኑ ሰአት ነዋሪው ህዝብ በአከባቢው ከሚገኙት ፌዴራል ፖሊስና አግኣዚ ሰራዊት ጋር ተፋጥጦ እንደሚገኝና፣ ከከተማ ሸሸመኔ በቅርብ
ርቀት ከምትገኘው ኦዶላ ተብላ ከምትጠራው ቀበሌ የሚገኘው የአግአዚ ወታሃደሮች ካምፕ መሆኑ የሚታውቅ ፅህፈት ቤት በሰልፈኞቹ መጋየቱና የፅህፈት
ቤቱ ንብረትም በጎደና በማውጣት እንዳቃጠሉት መረጃው ጨምሮ አሳውቀዋል።
በአሩሲ ከተማም የካቲት 08/2008ዓ/ም በመቀጠል ላይ ያለው ሃይለኛ ሰልፍ ለማቆም ፌዴደራል ፖሊስና አግአዚ ሰራዊት በሰልፈኞች ላይ የሚያስለቅስ
ጋዝ የመርጨት እርምጃ ቢቀጥሉም እንኳ፣ ሰልፈኞቹ ከቁጥጥራቸው ውጭ በመሆን በየእስር ቤቱ የሚገኙት እስረኞችም በሩን ሰብረው በመክፈት እንደፈቱና
የአስተዳዳሩ ፅህፈት ቤትም እንዳቃጠሉት ለማወቅ ተችለዋል።
በተመሳሳይ፣ በምስራቅ ሃረረጌ ዞን ጉራዋ ከተማ በተነሳው የህዝብ ቁጣ
የአግኣዚ ሰራዊት በከፈቱት ቶኩስ አንዲት የ60 አመት ሽማግለ ወ/ሮ ጁህራ ሙሳና ወጣት አደም መሃመድ የተባሉትን ንፁሃን ዜጎች እንደገደሉዋቸውና፣ በተጨማሪም ለሌሎች 3 ዜጎች ደግሞ በጥይት ተገድለው ማንነታቸው በማጣራት
ላይ መሆኑንና በአጠቃላይ በኦሮምያ በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ እየቀጠለ መሆኑን መረጃው በመጨረሻ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment