በአንዲት አገር ስልጣን ይዞ አገርና ህዝብ እያስተዳደርኩ ነኝ የሚለው ገዢው
መንግስት በአገሪትዋ ውስጥ የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶች የሁሉም ምንጭ እድገና ለውጥ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ለማሻሳል
የተለያዩ ጥናቶች በማካሄድ ከችግር አረንቋ ሊያላቅቅ የሚያስችሉ፣ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ የሚያመጡ ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች ሊነደፍ
ይችላል።
ለነዚህ ፕሮጀክቶች ለማስፈፀም በጀት በሚያጥርብት ጊዜ ደግሞ ከህዝብ ግልፅነት
ያለው መረዳዳት በመፍጠር፣ የይገባኛልና የመለከተኛል ወኔ በመፍጠር፣ ከዚህ በመነሳት በፍልጎትና ፍቃደኝነት የተመሮከሰ እንደየ አቅሙ
በገንዘቡ፤ በጉልበትና በእውቀቱ ሊያበረክት ይችላል።
ካለፈው ደግሞ ገዢው ስርአት ከውጭ ባንኮች ብድር በማስገባት በምን ላይ
እንደዋለ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገብገት ህዝብሊ ያውቀው በሚችል አኳኃን የመጨረሻ መንገድ በየጊዜው እያስረዳ ቢሄድ የት እንደዋለ
ግልፅ የሆንለታል።
በተጨማሪ ደግሞ የሚሰሩት ሜጋ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ ግንባታቸው
ጨርሰው ለአገልግሎት ሲበቁ፣ አንደኛ ትኩረታቸው በችግር ምክንያት ተጨማልቆና የኔነው በማለት ሁለንትናዊ አቅሙ በማበርከት እንዲሰራ
ያደረገው ህዝብ ምኞቱና ፍላጎቱ በሚገባ ተመልሶለት፣ ዘላቂ መፍትሄ በማግኘት ኑሮውን ከተደላደለና ከተረጋጋ በኃላ ከውጭ የሚገኝ
እገዛ ከሚመለከተውና የሃብቱ ባለቤት ከሆነው ህዝቡ ጋር በመሆን፣ ግልፅነት የለው መረዳዳት በመፍጠር ከተሰሩት ትላልቅ ፕሮጀክቶች
ከተሰሩለት አላማ አንፃር ሳይቃረን አለም አቀፍና የተመጣጠነ የሽያጭና ህጋዊ ዋጋ ውሎችን በማሰር፣ ከሱ ላይ ከሚገኘው የገቢ እዳ
ሊመልስና ለአገር ልማት ሊውል ይችላል።
እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉት ሙስና እንደ ባህል ቆጥረው የሚያስተዳድሩት መሪዎችና
ካድሬዎች የበዙባት አገር ግን፣ ህዝብ ወደ ተሻለው የኑሮ ደረጃና እድገት ሊያሸጋግሩ ይችላሉ በለህ መጠበቅ፣ ውጤቱ ባዶ ከመሆን
ባለፈ የሚጨበጥ ፍሬ ነገር የለውም።
በመሆኑ ደግሞ በእንዲህ ያለ የተዛባ አካሄድ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጊዜ ወደ
ጊዜ በማህበራዊ ኑሮ እየተጎሳቆለ እንደመጣና አሁንም እንደዛው እንዳለ ጥያቄ ውስት የሚያስገባ አይደለም።
መፍትሄ ካጡት የማህበራዊ አገልግሎት ችግሮች አንዱ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት
የሚመለከት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት በእለታዊ ኑሮው ላይ እየተጉላላና ከባድ ችግር እያሳለፈ የመጣና
ያለው ሆኖ፣ የሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ዘላቂ ምላሽ የሚሰጠው በማጣት ከዛሬ ነጌ በማለት ፀሃይ እየጠለቀችበት ያለ ብቻ ይሆን፣ የኢአዴግ
ባለ ስልጣናት በመላው አገሪቱ ያለው በሃይል እጥረት እየተሰቃየ የመጣና ያለው ህዝብ፣ በየጊዜው አካሂደናቸዋል ለሚሉዋቸው ግብአቶችና
የፕሮጀክት ስራዎች አመት ሳይሞላቸው ሲፈርሱና ሲበላሹ ማየት የተለመደ ተግባር ሲሆን፣
በሌላ በኩል ደግሞ የፋይናንስ እጥረት አጋጥሞብን፣
እንዲሁም በዘርፉ በቅርብ በሚሰሩ የመንግስት አካላት ላይ በሙስና ምክንያት ለመስሪያ ተብሎ የተበጀተውን ገንዘብ ስራ ላይ ሳይውል
ተጠፋፍቶ ወዘተ በሚል በየጊዜው ህዝብ በሚጠይቃቸውና በሚያማርራቸው የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠሩ መጥተው ብቻ ሳይሆን፣ የፕሮጀክቱ
መጨረሻ በማይታወቅ በሜጋ ፕሮጀክቶች ስም እየሰራን ነን በሚል ከህዝብ መጠኑ የማይታወቅ ብዛት ያለው ገንዘብ በመዋጮ ምክንያት በመሰብሰብ፣
ከዚ ባለፈም ከውጭ አገሮች በቢልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በማምጣት ፕሮጀክቱ ግማስ ያህል ሳይደርስ አሁን በኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት
በየቀኑ እየተሰቃየ ያለውን ዜጋ ተስፋው በመጥፋቱ ለፖለቲካዊ ጥቅሙ ሲል ከጎሮ ቤት አገሮች ጋር አለም አቀፍ መርህ ያልተከተለ ውሎችን
ሲፈራረሙ ይታያሉ።
የኢህአዴግ መሪዎች መቸ ተሰርቶ አገልግሎት ላይ ይውላል የሚለውን ሳያሳውቁ፣
ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠር ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ፕሮጀክት እየገነባች ነች እየተባለ፣ ህዝብ ያለ አንዳች ፍሬ ከተስፋ
ወደ ተስፋ ሊጓዝ የሚያስችለው መንገድ ስልት በመንደፍ ፕሮጀክቶቹ ሳይጨረሱ በእንጥልጥል ላይ እያሉ አሁን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ
ዜጋ በተለየየ ወጪዎች የሚደረግለት ግድብ ይሁን ሌላ ትናንሽ ፕሮጀክቶች፣ የፖለቲካ ንግድ እየነገዱ በህዝብ ትከሻና አደራ ቁማር
ሲጫወቱ ህዝብ ደግሞ በኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት ሲያማርር ገዢው ኢህአዴግ ደግሞ ውሎችን በማሰር ላይ ይገኛል።
No comments:
Post a Comment