የኢትዮጵያ ህዝቦች መራራ ተጋድሎ በተለይ ደግሞ
የትግራይ ህዝብ ስፋቱና ጥልቀቱ፤ ምሬቱንና ፅናቱን በአጠቃላይ ተፈጥሮኣዊና ሰው ሰራሽ መሰናክሎቹን ፈትሾና መርምሮ በቃላት ለመግለፅ
ከባድ ስለሆነ፣ የትህዴን ድርጅት የትግራይን ህዝብና አጋር ድርጅቶቹን ሐቀኛ ተጋድሎ ለሚመራመሩ ሊቃውንት በመተው ግንቦት 20ን
አስመልክቶ የሚከተለውን መግለጫ አቅርቧል።
የትግራይ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ከሁሉም ጭቁን የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በጋራ
በመሆን የውስጥና የውጭ ጠላቶቹን መክቶ ያሳፈረና ለብቻው ያለምንም ረዳት ማለቂያ የሌላቸው ጠላቶቹንና የውጭ ደጋፊዎቻቸውን በማሸነፍ
ባለድል የአርነት ዋልታን የተጎናፀፈ አኩሪ የታሪክ ህዝብ ነው።
ህዝባችን የግዕዝ መሰረት ሓበሻዊ ርስት የነፃነት ችቦ መጀመሪያ፤ የጥቁር
አፍሪካውያን ኩራት ግን ደግሞ የኢትዮጵያውያን መነሻ የሆነች ነፃ ሃገር ለዘላለም እንድትኖር በይበልጥ የትግራይ ህዝብ ከባድና መራራ
መስዋዕት እንደተከፈለበትና የኢትዮጵያ ህዝብ ዋልታ ሆኖ በግንባር ቀደምነት እንደሚገኝ የህዝባችን እልፍ ተጋድሎ ሐቀኛ ስእል ይመሰክራል።
ተተካኪ የባእዳውያን
ጌቶቻቸው ያልተለየው በአማራ ጭቁን ህዝብ ስም የሚሸቅጡ ገዥ መደቦች፤ የጃንሆይ ስርዓት መሳፍንቶች፤ተላላኪ ሰራዊታቸውና ፋሽስት
ደርግ ኢሰፓ ለትግራይ ህዝብ ባህሉንና ታሪኩን በመርገጥ ቋንቋውንና ክብሮቹን ንቀው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹን ገፈው በባርነት
ጨለማ ውስጥ በመክተት ከ61 ዓመታት በላይ በደሙ ውስጥ እንደመዥገር የጠበቁ የኢትዮጵያና የትግራይ ህዝብ ደመኞች እንደነበሩ የሚታወስ
ነው።
ከዚህ ከተገለፀውና ሌሎች ጭቆናዎች ለመላቀቅ ነው የትግራይ ህዝብ እስትራቴጂካዊ
የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ማለትም እንደ ኃይለ ስላሴ ስርዓትና ደርግ ኢሰፓ ለመደምሰስ አባቶቻችን አስቀድመው እነብላታ ሃይለማርያም
ያቀጣጠሉት እሳት በ1966 ዓ.ም በተነሳሽ የህዝብ ልጅ ተማሪዎች ማህበር ገስገስቲ ብሄር ትግራይ( ማ.ገ.በ.ት) በአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ተፀንሶ በየካቲት 11 1967 ዓ.ም የትግራይ ህዝብ ሓርነት ችቦ በደደቢት በረሃ የተለኮሰው።
ለውጥ ፈላጊው የትግራይ ህዝብ ትግል ከመጀመሪያ አሃዱ ብሎ ሲነሳ በክልሰ
ሃሳብና በተግብር ከባድ ፈተና እንዳለ አምኖ ወታደራዊ ስልቱ በተራዘመ ደፈጣዊ ስልት ወደ ፍፁም እስትራቴጂካዊ ስልት በመሸጋገር
ፖለቲካዊ ሳይንሱን በጎነፃዊና ጎነፃዊ ያልሆነ መሪ እየተከተለ ሰፊው ህዝባችን ይንቃ ይደራጅ ይታጠቅ፤ከሁሉም አጋር ድርጅቶች ዴሞክራሲያዊ
ሃይሎች እና ጭቁን ብሄሮች ትግላችንን እናጠናክረው በማለት ከጎረቤት ህዝቦችና መንግስት ጋር ሳይቀር ዝምድናውን በማጠናከር መራራ
ትግል አካሂዶ መራራ መስዋእት እየከፈለ መጨረሻ ወዳላገኘው የግንቦት 20 ድል ፍፃሜ የደረሰው።
የግንቦት 20 ድል በቀልድ እንደገና ጨዋታ የተገኘ ሳይሆን ሁሉም የኢትዮጵያ
ህዝብ ዋጋ የከፈለበት መራራና የረጅም ዓመታት የትግል መሰናክል የጠየቀ በመሆኑ በአይነቱ ድርብ በደሉንና ድርብ ዋጋው የትግራይ
ህዝብ ትግል ልዩ ያደርገዋል።
ከደደቢት በረሃ
እስከ ሞያሌ፤ከባዳ በራህለ እስከ ፈርፈር ሶማሌ ወደብ የ65 ሺህ ሰማእቶቻችን አጥንት ከ100 ሺህ በላይ ስንኩል ጓዶቻችን ፤ወንድም
እህቶቻችንና አባቶቻችን አጥንት ተከስክሷል። የጀግኖቻችን ደም በእያንዳንዷ የኢትዮጵያ ስንዝር መሬት ተቀብቶ የተለያዩ ቦታዎች ወድሞው ቤተሰቦቹን አጨልሞ በቢሊዮን የሚገመት የአገራችን ሃብት ወድሞ በመጨረሻ ደግሞ ደርግ ኢሰፓ
ለመጨረሻ ጊዜ ተደመሰሰ።
የትህዴን ድርጅት ሲካሄድ የነበረው ትግል የህዝብ ጥያቄ አቋሙ አገራዊ
ስለነበር ከየካቲት 11 1967 እስከ ግንቦት 20 1983 ዓ.ም በተካሄደ መራራ ተጋድሎ የተገኘ ሙሉ ያልሆነ ውጤት በኢትዮጵያ
ህዝብ ትግል መሆኑን ያምናል።
ይሁን እንጂ ይህ መራራ ትግልና መስዋዕት ሲገባ የነበረውን
ማለቂያ የሌለው ቃል ኪዳኖች ጥቂት ከዳተኞች በሰፊው ህዝብ ድጋፍ ወደ ስልጣን ኮረቻ የመጡት የወያኔ ኢህአዴግ ቡድን ተኩላዎች የግንቦት
20 ድልን ቀምተው በጀግኖች አጥንት ላይ በቆሙ ወንበሮች ተኮፍሰው ለህዝባችን ወደ ዳግም ባርነት ስለሚከቱት ትህዴን የህዝባችንና
የሰማእቶቻችንን ሐቀኛ ትግል እና መጨረሻ ያላገኘውን የግንቦት 20 ድል ፍፃሜ ለማደስና የህዝብን ታሪክ ለህዝብ ለማድረግ ዳግም
ትግል ወልዶ የትግራይ ህዝብና የትግዴን ድርጅት አሁንም ለወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት ቡድን ለማስወገድ ሁለንተናዊ ትግል አጠናክሮ በመገስገስ
ላይ ይገኛል።
ይህ በጊዜያዊ
አዋጅ ስም ሰአት እላፊ እያለ ዜጎቻችን ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ በገዛ መሬታቸው ቆርፍዶ በመያዝ ያለፍርድና ያለ ህጋዊ ዋስትና
ምህረት የሌለው እያፈነ የሚያጉራቸውና እየገደላቸው ያለው ወደ ስደት እንዲያመሩ እያደረገ ያለው አፋዊ የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት
በጭቁኖች ህዝባዊ ትግልና ሌሎች ዴሞክራሲያውያን ታጋዮች ግባተ መሬቱ የሚገባበት ሩቅ እንዳልሆነ አምኖ በፅናት በመታገል ላይ ይገኛል።
በመጨረሻ የትህዴን ድርጅት በግንቦት 20 ምክንያት ለመላ ለውጥ አንድነትና
ዴሞክራሲ ፈላጊ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የሚከተለውን መልእክት ያስተላልፋል።
የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት ጎርፍ ወደ ኩሬ እንደሚባለው እንደአመሉ በአፋዊ
ልሳኑ ህዝብን ከማደናገር አይቆጠብም በጥልቅ ተሃድሶ ስም ደግሞ ጅምላዊ ትርምስ እየቀጠለ ይገኛል። ስለዚህ መላ ህዝባችን በሁሉም
ዘርፍ ነቅተህና ተደራጅተህ በአገር ውስጥና በውጭ ክንድህን በማጠናከርና በመተባበር ዋነኛ ጠላትህን የወያኔ ኢህአዴግን እድሜ ለማሳጠር
ከመሪ ድርጅትህ ትህዴን ጎን በመሆን ትግልህን አጠናክረህ እንድትቀጥልበት ጥሪ እናቀርባለን።
ይህ የህዝባችንን የአመታት የትግል ፍሬ ቀምቶ የጀግኖች ሰማእቶቻችንን
አደራ ረስቶ በዳንኬራና ጉራ ለመብለጥ በየአይነታቸው ማደናገሪያ አጀንዳዎች እየከፈተ እየቀጠለ ቢሆንም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝባችን
ግን በድርቅ አለንጋና ስራ ኣጥነት አድሎኣዊ አስተዳደር እየተሰቃየ መሆኑ አለም የሚያውቀው እውነታ ነው። ስለዚህ ነው የትህዴን
ድርጅት የጉንበት 20 ድል ቀምቶው የህብን ዓላማ ክደው ሃገርን እያመሱ ያሉ ፀረ ህዝብ የሆኑ ገዢዎች በትግሉ ኣስወግዶ መና የቀረውን
የህዝብ ሁለንተናዊ ፍላጎትና ጥቅም ግቡን እንዲመታ በመረባረብ ላይ ይገኛል።
ክብርና ሞገስ ለጀግኖች ሰማእቶቻችን!
ድል ለጭቁኖች!
ትህዴን ግንቦት 20,2009 ዓ/ም
No comments:
Post a Comment