Friday, February 16, 2018

በአዲስ አበባ ዙሪያ ተቃውሞ በርትቷል፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአፍሪካ ሕብረት ሰራተኞች ባሉበት እንዲቆዩ ታዘዋል።



  የህዝብ ተቃውሞ አዲስ አበባ እየተካሔደ ሲሆን ሱሉልታ፣ ጣፎ፣ ቡልቡላ፣ ሀይሌ ጋርመንት መሥታወት ፋብሪካ፣ አየር ጤና፣ ቡራዬ ዙሪያውን የህዝብ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው።
  የፌደራል መንግስቱ መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ በመሐል ከተማ የስራ ማቆም አድማ እንደተካሄደባት መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በሰፊው የተተገበረው የዛሬው አድማ፣ በዋና ከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ሲተገበር ማየታቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

  እንደ እማኞቹ ገለጻ፤ በአዲስ አበባ ትልቁ የገበያ ስፍራ መርካቶ ውስጥ የንግድ መደብሮች ተዘጋግተው የዋሉ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎችም የታክሲ አገልግሎት ተቋርጦ ተስተውሏል፡፡ በዓለም-ገና፣ ካራቆሬ፣ አየር ጤና፣ ጆሞ፣ ሰበታ እና በሌሎች አካባቢዎችም የስራ ማቆም አድማ የተደረገ ሲሆን፤ በተጠቀሱት አካባቢዎች የንግድም ሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
  በካራቆሬ ኬንቴሪ በተባለው የከተማዋ ክፍል ደግሞ የአደባባይ ተቃውሞ ጭምር መደረጉን ከመረጃዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በሰልፉ ላይም ‹‹ወያኔ ሌባ!›› የሚል መፈኩር ሲስተጋባ መዋሉም ተነግሯል፡፡ ነዋሪዎች ሰልፍ መውጣታቸውን ተከትሎ ፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው መድረሳቸውና ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸውንም እማኞቹ ይናገራሉ፡፡

 

 

No comments:

Post a Comment