በደረሰን ዘገባ መሰረት አምባገነኑ የኢህአደግ ስርዓት በአፋር ክልል ውስጥ እጁን በማስገባት
የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የተቃወሙና ከስርዓቱ ጋር ሊጣጣሙ ያልቻሉ አንዳንድ የክልሉ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸውና ከመደበኛ ስራቸው
ተነስተው ከመረጣቸው ህዝብ ውሳኔ ውጭ እየተባረሩ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል፣
በክልሉ ከሃላፊነታቸው ከተነሱት ባለስልጣናት መካከል።-
1-አቶ መሓመድ ሙሳ የፋንቲራሱ ዞን ፤ ጉሌና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩ
2-አቶ ዓብዱ ሃይሳማ የቢዱ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩ
3-አቶ አህመድ ሓሰን የፋንቲራሱ ዞን አብዴታ ጽ/ቤት ኅላፊ የነበሩ
4-አቶ ኢብራሂም መሃመድ የቴሩ ወረዳ የአብዴፓ ጽ/ቤት ኅላፊ የነበሩ
5-አቶ ላዖይታ መሓመድ በጋቢሩሉ ዞን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩ ሲሆኑ በአሁኑ
ግዜ በግለሰቦቹ ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ታውቋል ፣
በተመሳሳይ መልኩ ጸረ-ዴሞክራሲው የኢህአደግ መንግስት በአፋር ክልል በቢዱና ኩሪ በተባሉ
ወረዳዎች ኗሪ የሆኑ ቁጥራቸው ከ 40 በላይ የአገር ሽማግሌዎችንና ወጣቶችን በማፈን በአሳይታ በሚገኝ እስር ቤት አስሮ እያሰቃያቸው
ሲሆን የሰዎቹን መታሰር ምክንያት በግልጽ የታወቀ ነገር ባይኖርም በስርዓቱ የተፈጠረ አጠቃላይ ውስጣዊ አለመተማመን ሊሆን እንደሚችል
የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል ፣