ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር
ከጀመረ ጥቂት አመታት ያስቆጠረ ሆኖ ባሳለፍነው ሳምንት ለዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ የሆኑ ተመራቂ ተማሪዎችን አስመርቋል ።ይህ በንዲህ
እያለ መንግስት ለመንገድ ልማት በሚል ሰበብ የሞስሊሙን ማህበረሰብ
ሳያማክርና ይሁንታ ሳያገኝ የሞስሊም መካነ መቃብርን በማንአለብኝነት በማፈራረሱ ምክንያት በከተማዋ ለተከታታይ ቀናት ህዝባዊ ተቋውሞ
ይካሄድ ስለነበር ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዩኒቨርሲቲው ግቢ የተማሪዎች ተቋውሞ ይቀሰቀሳል የሚል የሰጋት ያደረበት የዩኒቨርሲትው
አስተዳደር የምረቃ ስነስርዓቱን ከተያዘለት ፕሮግራም ቀደም ብሎ እንዲፈጸም ለማድረግ ተገድዷል ሲሉ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ይደመጣሉ ።
በምረቃው ስነስርዓት በዩኒቨርሲቲው ተገኝቶ
ለተመራቂ ተማሪዎች ዲፕሎማ የሰጠ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መሆኑ ቷውቋል ።
ሁኔታው የኢህአደግ ስርዓት ከመቸውም
ግዜ በላይ ከህዝብ መነጠሉንና ስጋት ላይ መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲሉ አንዳንድ የከተማዋ ኗሪዎች ይገልጻሉ ።