የኢህአደግ መንግስት የተለያዩ ሞያዊ ስልጠና ይሰጣቹሃል በሚል ማታለያና ቅስቀሳ በርካታ ወጣቶችን ወደ ውትድርና
ሞያ እንዲገቡ ካደረገ ብሁዋላ ፤ በሰላም አስከባሪነትና አሽባሪዎችን ለመምታት በሚል ሰበብ በሶማሊያና በዳርፉር በማይመለከታቸው
ውግያ የማገዳቸው ወጣቶች ደም ሳይደርቅ በቅርብ ግዜ ደግሞ ቀይ ባህርን አቋርጦ ወደ የመን ወታደሮች መላኩን ለማወቅ ተችለዋል፣
በዘመነ መለስ ዜናዊ ሃያላን ሃገራት ለማስደሰት ሲባል በ 10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በሶማሊያ
በማይመለከታቸው ውግያ ገብተው መገደላቸውና ሬሳቸውንም መጎተቱ እንዳይበቃ ፥ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ በሃ/ማሪያም ደሳለኝ መሪነት
ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን ወደ የመን መላካቸው ብዝዎችን እንዳሳዘነና በተለይም ጉዳዩ በሃገራቸውና በህዝባቸው በሚቆረቆሩ የመከላከያ
ሰራዊት አባላት መካከል እጅግ አነጋጋሪ እየሆነ መምጣቱ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣
ይህ በእንዲህ እያለ ለብዙ አመታት ያገለገሉ መኮንኖችና ሌሎች የሰራዊት አባላት በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ
በተፈጠረው አለመተማመን ምክንያት ከ 19ኛ ክ/ጦር በርካታ ወታደሮች መባረራቸውን ቷውቋል፣
ከተባረሩት የሰራዊት አባላት መካከል፣
1-ወዲ ጉዖይ ፤ በሰላም አስከባሪ ስም ወደ ዳርፉር ተልኮ የነበርና የ 19ኛ ክ/ጦር አዛዥ የነበረ
2-ሻለቃ በርሀ ታፈረ(በርሀ ጅግና )
3-ሻለቃ ገሰሰ ግደይ
4-ሻምበል አበበ
5-መሓመድ ኻልድ
6-ተስፋይ
7- በርሀ ሃፍቱ …ሲሆኑ የማባረሩ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ ከክ/ጦሩ ያፈተለከ መረጃ ያስረዳል
፣