በክልሉ የሚገኙ ነጋዴዎች በጥናት ያልተደገፈና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ከፍተኛ ግብር ተገደው እንዲከፍሉ
የተደረገ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም በአሁኑ ግዜ በየአከባቢው የሚገኙ የመንግስት የመስተዳድር አካላት ነጋዴውን መክፈል ከሚገባው በላይ
ከፍተኛ ግብር ያስከፈሉት የበታች ሃላፊዎች ናቸው ብለው መናገር ጅምረዋል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት በመቐለ ከተማ የዓይደር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ገብረመድህን ወልደ አረጋይ በክፍለ
ከተማው ለሚገኙ ተሰሚነት አላቸው የሚባሉ ታላላቅ ነጋዴዎችን ስልክ እየደወለ ከፍተኛ ግብር እንድትከፍሉ የተደረገው በክ/ከተማው
ንግድና ኢንድስትሪ ቢሮ ሃላፊዎች አቶ አማኒኤልና አቶ አለምሰገድ ብቸኛ ውሳኔ ነው። ተበድለናል የምትሉ አቤቱታችሁን በፅሁፍ ማቅረብ ትችላላችሁ በማለት ነጋዴውን ለማምታት እየሞከሩ
ነው።
በወቅቱ
አቤት ብሎ መልስ ያጣው የንግዱ ማሕበረሰብ አሁን የመንግስት የመስተዳድር አካላት ለማስመሰል በስልክ እቤቱ ድረስ እየደወሉ በግብር
አከፋፈል ዙርያ ቅሬታ ካላችሁ በፅሁፍ ማቅረብ ይቻላል እያሉ ነጋዴውን መወትወት የነጋዴውን ችግር ለመፍታት ፍላጎት ኖሯቸው ሳይሆን
በመጭው ሚያዝያ 2005 ዓ/ም ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ ከወዲሁ ድጋፍ በማሰባሰብ የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም የሚደረግ
ከንቱ ሙከራ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ።