በአሁኑ ግዜ አምባገነኑ የኢህአደግ መንግስት አዳዲስ ምልምሎችን ለመመልመል እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም መንግስት
ለሃገራቸው ክብር ህይወታቸውን የከፈሉ ወታደሮች ቤተሰቦችና በአውደ ውግያ ቆስለው በተረፉ የሰራዊት አባላት ላይ ያለው አያያዝ ጥሩ
ባለመሆኑ መንግስት ወጣቱን ለመመልመል ያደረገውን ጥረት ተቀባይነት እንዳላገኘ ቷውቋል።
ወደ ቤተሰቦቻቸው
በፈቃድ ወይም ፈቃድ ሳያገኙ ሄደው ሳይመለሱ የቀሩትን የሰራዊት አባላትን ይዘው እንዲያስረክቡ የታዘዙ የተለያዩ አከባቢ የፖሊስ
አዛዦች መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ደስተኞች እንዳልሆኑና ከህዝብ ሊያጣላን ነው የሚል ተቋውሞም ውስጥ ለውስጥ እንደሚነገር ለማወቅ
ተችለዋል።