በአማራ ክልል ፤ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፤ በወንበርማ ወረዳ ፤ በሽለንዲ ከተማ ኗሪ የነበረው አቶ ይሁን
ደምመላሽ ታሕሳስ 11,2005 ዓ/ም ከቀኑ 8፣00 ሰዓት በከተማዋ የጸጥታ ሃላፊና ሌሎች ሦስት ፖሊሶች በተተኮሰበት ጥይት አናቱ
ላይ ተመቶ ህይወቱ ማለፉን ቷውቋል ።
ሟቹ ግለሰብ ፤ አሸባሪ በሚል ሰበብ ፤ በአምባገነኑ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች በተተኮሰበት ጥይት በግፍ
የተገደለ ሲሆን፥ የቀብር ስነስርዓቱ ታህሳስ 12, 2005 ዓ/ም ከቀኑ 6፣00 ሰዓት በቁጪ ወረዳ ተፈጽሟል ።
በአሁኑ ጊዜ በአቶ ደምመላሽ መገደልና በአጠቃላይ በአከባቢው ኗሪዎች ላይ እየተፈጸመ ባለው ግፍ ስጋት ያደረባቸው
የከተማዋ ኗሪዎች ጉዳዩን ወደ እሚመለከታቸው የክክል የመንግስት አካላት ለማቅረብ ስምንት አባላት ያሉት አንድ ኮሚቴ አቋቅመው በመንቀሳቀስ
ላይ መሆናቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል ።