Sunday, December 23, 2012

በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን ፤ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ፤ የከተማው የፋይናንስ ሰራተኛ የነበረ አቶ አፍወርቂ የተባለ ግለሰብ ሙስናን በመቃወሙ ምክንያት ከመደበኛ ስራው እንዲነሳ ተደርጓል።



የሽሬ እንዳስላሴ ከንቲባ አቶ ፍስሓ ውበት ከህዝብ በተለያየ ምክንያት የተሰበሰበውን ገንዘብ ለግል ጥቅሙ ማዋል ስለፈለገ አፍወርቂ የተባለውን የፋይናንስ ሰራተኛን ለህጋዊ ስራ ወጪ ያልሆነውን ገንዘብ ወጪ ሆኗል በማለት እንዲፈርምበት ያስገድደዋል ፥ የፋይናንስ ሰራተኛውም ህጋዊ አለመሆኑን ገልፆ፤አልፈርምም ይላል ።የተሰጠውን መመሪያ ተቀብሎ ባለመፈረሙም እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በከተማው ከንቲባ ቀጭን ትእዛዝ ግለሰቡ ከስራው እንዲነሳ መደረጉን ለማወቅ ተችለዋል።
የኢህአደግ መንግስት ነጋ ጠባ ሙስናን እዋጋለሁ የሚል መፈክር ቢያሰማም በተግባር ግን ሙስናን የሚዋጉ ፤ ለሃቅና ለፍትህ የቆሙትን ዜጎች ከሃላፊነታቸው ሲያስነሳ እንጂ ሞሶኞቹን ሲዋጋ ሆነ ወደ ህግ ሲያቀርብ አይታይም።