Sunday, January 13, 2013

የፊታችን ሚያዝያ 2005 ዓ/ም በአገር ደረጃ በሚካሄደው የአከባቢና የሟሟያ ምርጫ የትግራይ ህዝብ የምርጫ ካርድ ባለመውሰድ በስርዓቱ ላይ ያለውን ተቃውሞ በመግለጽ ላይ ይገኛል።




ጥር 2,2005 ዓ/ም የስርዓቱ ካድሬዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሽረ እንዳስላሰ ከተማ ኗሪ ህዝብን የምርጫ ካርድ እንዲወስድ የተለያዩ ቅስቀሳ ቢያደርጉም እስካሁን ድረስ ካርድ የሚወስድ አንድም ሰው እንዳልተገኘ ቷውቋል።
ኢህአደግ የኢትዮጵያ ህዝብንና የዓለም አቀፍ ሕብረተሰብን በማምታታት ዴሞክራሲያዊ መስሎ ለመታየት ሲል ሚያዝያ 2005 ዓ/ም ለማካሄድ ያቀደው የይስሙላ ምርጫ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሊሆን እንደማይችል ህዝቡ ቀድሞ በመገንዘቡ ከወዲሁ መቋወም ጀምሯል ። የሽረ እንዳስላሰ ከተማ ኗሪዎች ያሳዩት የምርጫ ካርድን ያለመውሰድ ተቋውሞ ህዝቡ በሚደረገው ምርጫ እምነት ማጣቱን የሚያመላክት ነው።