በትግራይ ማእከላዊ ዞን ፤ በታሕታይ ማይጨው ወረዳ ፤ የዓቃቢ ሰዓት ጣብያ አስተዳዳሪ አቶ ኪዳነ ገብረተንሳይ
የተባለ ካድሬ የኣካባቢውን ገበሬዎች በበጋው ወራት ላይጠቀሙበት አንዱን ኪሎ ማዳበርያ በ10 ብር ሂሳብ እንዲወስዱ እያስገደዷቸው
መሆኑ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት ማዳበርያ በዚህ ግዜ አያስፈልገንም አንገዛም ብለው የተቋወሙ ገበሬዎች ወደ ካድሬው
ቀርበው ማስጠቀቅያ እንዲሰጣቸው ከተደረገ በሁዋላ ያለፍላጎታቸው እንዲወስዱ ተገደዋል። የህወሓት ታጋይ የነበረ ሓጎስ ብርሃነ የተባለ
አንድ ዜጋ ማዳበርያ አያስፈልገኝም ፍላጎታችሁ ገንዘብ ከሆነ ያውላችሁ መውሰድ ትችላላችሁ ብሎ በመናገሩ ብቻ እንደ አንድ ወጀለኛ
ተቆጥሮ እስር ቤት እዲገባ መደረጉን ለማወቅ ተችለዋል።