በደረሰን ዘገባ መሰረት አብዛኛዎቹ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ከሄዱት የ 31ኛ ክ/ጦር የ
1ኛ ሬጅመንት አባላት ወደ ምድብ ቦታቸው ስላልተመለሱና አንዳንዶችም ወደ ተቋዋሚው ጎራ ተቀላቅለዋል በሚል ሰበብ በሬጅመንቷ በየደረጃው
በሚገኙት የሰራዊቱ አመራሮች ላይ የማእርግ እድገት እገዳ መደረጉን ለማወቅ ተችለዋል።
የማእርግ እድገት ደረጃ እገዳ ከተደረገባቸው የ 1ኛ ሬጅመንት አመራሮች መካከል መ/አ ታፈረ የሬጅመንቷ
የሞርታር ምድብ አመራር የነበረና ወደ ተቋዋሚው ጎራ የተቀላቀለ ፤
‘ወዲ አማረ’ በሚል የሚታወቅ ፲/አ ደምበለ ወደ ቤተሰቡ ፈቃድ ሄዶ ያልተመለሰና ሌሎች በርካቶች ይገኝባቸዋል ።
በመከላከያ
ሰራዊት ውስጥ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ በመሄድ ላይ ያለውን ብልሹ አሰራር ምክንያት በስርዓቱ ላይ እምነት ያጡ የሰራዊቱ አባላት
በየግዜው የጦር ክፍላቸውን በመክዳት እደሚጠፉ የሚታወቅ ነው።