በጥልቅ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ላይ አተኩሮ የሚሰራ ከሃገረ ጣልያን በመጣው ካዲስኮ በተባለ በሞያው
ከፍተኛ ልምድ ያለው ድርጅት ከወሃ ሃብትና ኢነርጂ ለመጡ ተሳታፊዎች ትምህርት እየሰጠ ቢሆንም ለመጠጥ ወሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ተብሎ
የሚመደበው በጀት በስርዓቱ ባለስልጣናትና ከነሱ ጋር ግንኝነት ባላቸው በሞያው የተሰማሩ ባለሞያዎች ስለሚባክን ከድርጅቱ የተገኘውን
ልምድ በስራ ላይ ለማዋል ያስቸግራል ሲሉ ይደመጣሉ።
በሃገሪቱ የሚታየው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት መፍትሄ የሚያገኘው ፤ አሁን የተገኘው ልምድም ተግባራዊ
የሚሆነው በአንድ ወቅት በስብሰባ በሚቀርቡ የጥናት ወረቀቶች ላይ በመወያየት ብቻ ሳይሆን በተግባር ሙስናን ማስወገድና ፍትሃዊ አሰራርን
ማስፈን ስቻል ነው በማለት ተሳታፊዎቹ ጨምረው ገልጸዋል።