የመቐለ ከተማ የመንገድ ትራንስፖርት ሃላፊ ኣይተ መድሃንየ ገብረስላሰ የተመራ በከተማዋ በሚገኝ የቴክኒክና
ሞያ ማእከል አዳራሽ በተካሄደው ስብሰባ 150 ኮንትራክተሮች የተገኙ ሲሆን በስብሰባው በከተማዋ እየታየ ላለው የህንጻዎችና የመንገድ
ግምባታ ጥራት አለመኖር ችግር መንስኤ ለመገምገም በተያዘው አጀንዳ ኢንጂነሩ ችግሩ የኮንትራክተሮች ብቻ አድርገው ለማቅረብ በመሞከራቸው
ተሰብሳቢዎቹ በቀረበው ሃሳብ አለመስማማታቸውን ቷውቋል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት ኮንትራክተሮቹ በከተማዋ እየታየ ላለው የህንጻና የመንገድ ግንባታ ጥራት ችግር መንግስትንም
ተቋራጨቹንም የሚመለከት ሆኖ በዋናነት ግን በዚሁ ጉዳይ ተጠያቂው መንግስት መሆኑን ጠቅሰው ይህም በጨረታ አሰጣጥና የስራው ሂደትን
በመከታተል ረገድ ባለው የአሰራር ክፍተት ሊገለጽ ይችላል።
Ø ሙስና በከፍተኛ ደረጃ በመንሰራፋቱ።
Ø ሁሌም አንድን ጨረታ አሸነፈ ተብሎ ኮንትራትን የሚረከብ ኮንትራክተር በሁሉም መመዘኛ ብቃቱ የሌሌው በመሆኑ
።
Ø በኮንትራክተሮች ተብየዎች እየተሰራ ያለውን ስራ በቀጥታ የሚከታተሉ የመንግስት አካላት በሙስና የተጨማለቁ
መሆናቸው።
Ø በየመንግስት መ/ቤት የተሰገሰጉ የመንግስት ባለስልጣናት ከኮንትራክተር ተብየዎች ጋር በመመሳጠር ስለሚያገኙት
ገንዘብ እንጂ ለሚሰራው ስራ ብዙም ትኩረት ስለማይሰጡ ።
Ø ህጋዊና ግልጽ የጨረታ አሰራር ባለመኖሩ ብቃቱ ያላቸው ኮንትራክተሮች በተለያየ መንገድ ከጨዋታ ውጭ ስለሚደረጉ።
ለመሳሰሉት ችግሮች ተጠያቂው መንግስት መሆኑና ቀደም ሲል በመቐለ ከተማ በ 6 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘላቸው
ፕሮጀችቶች አለመተግበራቸውን በመጥቀስ መንስግት በመወከል ስብሰባውን ለመምራት የተላከው ኢንጂነር መድሃንየ ገብረስላሰ የችግሩን
መንስኤ በትክክል ከመመልከት ይልቅ አቅጣጫውን በማስቀየር የመንግስትን ችግር ለመደበቅ በመሞከሩ ተሰብሳቢዉቹ ሳይስማሙ ስብሰባው
መበተኑ ከስብሰባው ተሳታፊዎች የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።