Tuesday, January 15, 2013

በመከላከያ ሰራዊት ፤ ከማእከላዊ እዝ ብቻ በየቀኑ ከ 40 በላይ ወታደሮች እንድሚከዱ በእዙ በተካሄደው የከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ስብሰባ ላይ ተገለጸ።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች መክዳታቸው የተገለጸው በሌትናል ጀንራል ኣበባው ታደሰ፤በብርጋዴር ጀነራል ይብራህ ዘሪሁንና በኮሌኔል ወዲ መስፍን የተመራ በሁለት ቦታ ተከፍሎ በተካሄደው ከቦጦለኒ አመራሮች በላይ የተሳተፉበት የ 6 ወራት የስራ ግምገማ ሲሆን የስብሰባው ዋና አጀንዳም በእዙ ውስጥ በከፍተኛ ቁጥር እየታየ ያለውን የሰራዊት መክዳት ለመገምገም ነበር። ከማእከላዊ እዝ ብቻ በየቀኑ ከ 40 በላይ ወታድሮች እንደሚከዱ በግምገማው ወቅት መገለጹን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት ስብሰባው ጥር 3,2005 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት በተከታታይ የተካሄደ ሲሆን ግምገማው እስከ ታች የሰራዊቱ አባላት ድረስ ወርዶ እንዲቀጥል በስብሰባው ማጠቃለያ መመሪያ መሰጠቱን ቷውቋል።
ከማእከላዊ እዝ ብቻ ሲከዱ ተገኝተዋል በሚል ከ 2000 በላይ ወታደሮች በሽረ እንዳስላሰ በእስር ላይ እንደሚገኙ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።