Tuesday, January 15, 2013

በአላማጣ ከተማ በእንዳ-ኪዳነ ምህረት ገርባ በተባለ አከባቢ ‘ህገ ወጥ የቤት ግምባታ’ በሚል ሰበብ ቤታቸው እንዳይፈርስ መንግስትን የተቋወሙ ወገኖች በፌደራል ፖሊስ ተይዘው እየታሰሩ መሆኑ ቷውቋል።

አምባገነኑ መንግስት ጥር 1/2005 ዓ/ም የራያ አላማጣን ህዝብ ወደ ልማት ስራ በሚል በተንኮል በማንቀሳቀስ ከበስተጀርባው  በልማት ስራ የተሰማራውን ህዝብ መኖርያ ቤት በህገ ወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶች ናቸው በሚል ሰበብ አፍራሽ ግብረ ሃይል ወደ አከባቢው በመላክ ቤቶችን ማፈራረስ ሲጀምር በአከባቢው ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ በመቀስቀሱ ምክንያት በመንግስት የተያዘው እቅድ ሙሉ ብሙሉ ተግባራዊ ሳይሆንይ መክሸፉን የሚታወቅ ነው።
በአከባቢው የተከሰተው ህዝባዊ ተቋውሞን ተከትሎ በርካታ የቤታቸውን መፍረስ የተቃወሙ የከተማ ኗሪዎች በስርዓቱ የፌደራል ፖሊስ ተይዘው እስር ቤት እንዲገቡ ተደርጓል።
በእስር ላይ ከሚገኙት የከተማዋ ኗሪዎች መካከል ፦
1-አቶ ገብረህይወት ጸጋይ
2-አቶ ሽለሺ አለሙ
3-አቶ አሰፋ አስገደ
4-ወ/ሮ ሽዋየ ከበደ
5-ወ/ሮ አረጋሽ
6-አቶ አሰፋ ዳርጌ
7-አቶ አባተ አለሙ ከነልጃቸው ሲሳይ አባተ
8-አምባቸው ሽፈራው
ሲሆኑ ግለሰቦቹ ማይጨው ከተማ ወደ እሚገኘው እስር ቤት ተወስደው ታስረዋል። መንግስት በኗሪዎቹ ላይ እየወሰደው ያለ እስር ቤት ውስጥ የማስገባት እርምጃ ቀጣይ መሆኑ ከአከባቢው የፖሊስ አባላት ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ያስረዳሉ።