Sunday, January 13, 2013

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፤ በማንኩሽ ወረዳ በመገንባት ላይ ባለው የአባይ ግድብ በጥበቃ ስራ ላይ የተሰማሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ታህሳስ 30/2005 ዓ/ም ያካሄዱት ስብሰባ ያለውጤት ተበተነ።




ስብሰባው የተመራው በዲቪዥን ኮማንደር አበበ ሲሆን በስብሰባው እንደ አጀንዳ የተነሱ ነጥቦች ፤ አባላት ለምን የተሰጣቸውን ስራና ሃላፊነት ጥለው ይሄዳሉ? ፤ በምናካሂደው እንቅስቃሴ ሁሉ ሚስጥር ለምን ይባክናል ? የሚሉ ይገኙባቸዋል። ስብሰባው ከሌሊቱ 10፣00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2፣00 ሰዓት ድረስ የቀጠለ ሲሆን በስብሰባው መጀምሪያ ተራ የፖሊስ አባላት በተነሱት ነጥቦች የሰጡት አስተያየት ሆነ ሃሳብ እንዳልነበረ ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ በንዲህ እያለ ተሰብሳቢዎቹ በስብሰባው የቀረበውን አጀንዳ ወደ ጎን በመተው በማህበራዊ ኑሮ ፤ የፖሊስ አባላት ፈቃድ ለምን ይከለከላሉ ? የፖሊስ አባልት ለሚያቀርቡት ማንኛውንም ጥያቄ በውቅቱ ተገቢ መላሽ ለምን አይሰጥም? የሚሉ ያልተጠበቁ የራሳቸው ጥያቄዎችን በማንሳት ስብሰባውን ሲመራ ለነበረው ኮማንደር አበበን አፋጠውታል። በዚህ ምክንያት ሳይግባቡ ስብሰባው መበተኑ ቷውቋል።