Sunday, January 13, 2013

የኢህአደግ መንግስት በሃገሪቱ ውስጥ የሃይማኖት ነጻነት እንዲጠበቅ በጠየቁ የሞስሊም ህብረተሰብ አባላት ላይ እየፈጸመው ያለ ግፍ አጠናክሮ ቀጥሎበታል።




ከአንድ አመት በፊት በእስልምና እምነት ተከታዮች በአወልያ ት/ቤት የተጀመረው ‘የሃይማኖት ነጻነት’ ይከበር ጥያቄ በአሁኑ ግዜ መላ አገሪቱን አዳርሶ ስርዓቱን ጭንቀት ውስጥ ከቶታል ። በሁኔታው ክፉኛ የተደናገጠው የኢህአደግ ስርዓት ንጹሃን ወገኖቻችንን አሸባሪዎች የሚል ስም በመለጠፍ ለአይናቸውንም ቢሆን ፍጹም አይተውት የማያውቅቱን ኮምፕዩተራይዝድ የሆነ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ይዘው ተገኝተዋል በሚል ሰበብ በማፈን ደብዛቸውን በማጥፋት ላይ መሆኑ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት ከአክራሪዎችና አሸባሪዎች ጋር ግንኝነት አላቸው የሚል ሰበብ በመፍጠር ከ አ/አበባ ከተማ ብቻ 110 ንጹሃን ዜጎች በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ቷውቋል።
በተመሳሳይ መንገድ፤ መንግስት ታህሳስ 23,2005 ዓ/ም በሃገሪቱ ውስጥ ከምሴ የአሸባሪች ማሰልጠኛ ማእከል ሆና እንደተመረጠች አስመስሎ ለፓርላማ ሪፖርት ካቀረበ በሁዋላ ፤ ከ 290 በላይ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ከያሉበት ታፍነው ተወስደዋል።