በደረሰን ዘገባ መሰረት የክልሉ ኗሪ ህዝብ የምርጫ ካርድ የመውሰድ ግዴታ እንዳለበትና ግዴታውን በማይወጣ
ማንኛውም ኗሪ ላይ፤ የኑሮ ውድነትን ለማርገብ በሚል በመንግስት ድጎማ ለህዝቡ በተመጣጠነ ዋጋ በሚቀርቡ የምግብ ዘይት ፤ ስንዴ በመሳሰሉት መሰረታዊ ሸቀጦችን
እንዳይገዛ እገዳ እንዲደረግበት መወሰኑን ቷውቋል።
በሽረ እንዳስላሰ ከተማ እየታየ ባለው የምርጫ ካርድ ያለመውሰድ እምቢተኝነት ጋር ተያይዞ በከተማዋ ህዝባዊ
ተቃውሞ ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት ያደረበት የክልሉ መንግስት ወደ አከባቢው ተጨማሪ አንድ መቶ የፌደራል ፖሊስ አባላት መላኩን
ለማወቅ ተችለዋል።
አመታት ያስቆጠረ የሽረ እንዳስላሰ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር የመንግስት ድጋፍ ታክሎበት ይፈታል
በሚል እምነት የከተማዋ ኗሪዎች የሚፈለግባቸውን ገንዝዘብ አዋጥተው በጀት ተይዞ የነበረ ቢሆንም ፤ የተመደበው ገንዘብ በስርዓቱ
ካድሬዎች ስለባከነና የከተማዋ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እስካሁን ድረስ መፍትሄ ስላላገኘ የከተማዋ ኗሪዎች አሁንም በከፍተኛ
ችግር ላይ ይገኛሉ።