Friday, January 18, 2013

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ጥር 4/2005 ዓ/ም ከቀኑ 12 ሰዓት በግቢው ተማሪዎች መካከል ሃይማኖታዊ ግጭት መከሰቱን ቷውቋል።

በደረሰን ዘገባ መሰረት የግጭቱ ዋና መንስኤ በሴቶች መኝታ ቤት ግድግዳ ተሰቅሎ የነበረ የቅድስት ማሪያም ምስል ከቦታው ተነስቶ ተቀዳድዶ በሽንት ቤት ውስጥ ተጥሎ በመገኘቱ በድርጊቱ የተቆጡ በዩኒቨርሲቲው የሚማሩ የኦርተደኩስ እምነት ተከታዮች በእልምናና በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ላይ ድንጋይ መወርወር በመጀመራቸው መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
በተፈጠረው ግጭት በበርካታ ተማሪዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ግጭቱን ትከትሎ በፌደራል ፖሊስ የተያዙ ቁጥራቸው ከ 400 በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በጅማ ከተማ በተለምዶ ፈረንጅ አራዳ እየተባለ በሚጠራው አከባቢ በእስር ይገኛሉ።
በዩኒቨርሲትው ግቢ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተስማርተው ጥበቃ በማድረግ ላይ ናቸው።