በከተማዋ የሚገኙ የኮለጅ ትምህርታቸውን በአግባቡ ተከታትለው በዲፕሎማና በዲግሪ የተመረቁ ወጣቶች የኢህአደግ
ስርዓት በሚከተለው የፖለቲካ ወገንተኝነት ምክንያት የገዥው ፓርቲ አባላት የሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች በቀጥታ በስራ ሲመደቡ አባላት
ያልሆኑት ግን ተደራጅተው ስራ እንዲፈጥሩ በወረዳዋ አስተዳዳሪ መልስ እንደተሰጣቸው ቷውቋል።
ባሁኑ ግዜ በየትኛውም የሃገሪቱ ክልል አንድ ዜጋ የመንግስት ስራ ማግኘት የሚችለው በብቃቱ ተወዳድሮ ሳይሆን
ከገዥው ፓርቲ ባለው ቅርበት ተመዝኖ ነው ። የገዥው ፓርቲ አባል ያልሆነ ሁሉ ስራ ስለማያገኝ ወጣቱ በሃገሩ ሰርቶ የመኖር ተስፋው
ጨልሞ የአደንዛዥ እጽ ተገዥ እየሆነ መጥቷል።
የወረዳዋ
ወጣቶች እንዲህ አይነቱ ተግባር በመላ አገሪቱ የሚሰራበት የገዥው ፓርቲ የተለመደ አሰራር በምሆኑ መፍትሄ ሊገኝ የሚችለው ሁሉም
ኢትዮጵያዊ ወጣት የኢህአደግን ስርዓት በማስወገድ በምትኩ የህግ የበላይነት የሰፈነበት ፤ አድልዎ ተወግዶ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ
መብቶች የሚከበሩበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሲመሰረት መሆኑ አውቆ ስርዓቱን በተግባር መቃወም ሲችል ነው ሲሉ መግለጻቸው ከቦታው የደረሰን
ዘገባ ያስረዳል።