አቶ አያሌው በየነ የተባሉ የዓረና ትግራይ አባል ፤ ከሽሬ እንዳስላሴ ወደ ሸራሮ ከተማ በመሄዳቸው ብቻ
እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው በከተማዋ የፖሊስ አባላት ተይዘው በእስር እንዲቆዩ ከተደረገ በሁዋላ ለቀዋቸዋል ።ሁኔታው በሚያዝያ ወር
2005 ዓ/ም በሚካሄደው የአከባቢና የከተማ ምርጫ ኢህአደግ እንደተለመደው ብቻውን ሮጦ አስሸኒፌአለሁ ለማለት የሚያደርገው ጸረ-ዴሞክራሲ
ተግባር ነው ሲሉ አንዳንድ ወገኖች ይገልጻሉ።
ይህ በእንዲህ እያለ በማይካድራ ከተማ በዓረና ትግራይ ጽ/ቤት አቅራቢያ ተተክሎ የነበረ የዓረና ትግራይ
ታቤላም በላው ላይ የነበረውን ጽሁፍ በቀለም በመደምሰስ ከቦታው ነቅለውታል ።እንደዚሁም የማይካድራ ከተማ በከተማዋ የዓረና ትግራይ
ተወካይ አቶ መረሳን በተደጋጋሚ እቢሮው ድረስ እያስጠራ ለማስፈራራት እንደሞክረ ቷውቋል።
በተመሳሳይ እንዲህ ዓይነቱ ተግባራት በደቡባዊ ምስራቅ ትግራይ በሰሓርቲ ሳምረም ከተማ የዓረና ትግራይ ተወካዮች
ላይ መፈጸሙን ለማወቅ ተችለዋል።