አደጋው በተከሰተበት ቦታ የነበሩ ሰዎች እንደገለጹት ከሆነ ጉዳት የደረሰባቸው እስረኞች አንዳንዶቹ የፍርድ
ቤት ቀጠሮ የነበራቸው ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግም የተፈረደባቸው ነበሩ ። በተከሰተው አደጋ አንዲት ነብሰ ጡር ሴት የምትገኝባቸው አምስት
ሲሞቱ በ 16 እስረኞች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ቷውቋል ።
በእስረኞቹ ላይ የከፋ አደጋ ሊደርስ የቻለው በአከባቢው የተመደቡ የእሳት ማጥፍያ መኪናዎች ባለመኖራቸው
ሲሆን መንግስት የእሳት ቃጠሎ በአከባቢው በተደጋጋሚ የሚነሳ መሆኑ እያወቀ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ከወዲሁ ለመከላከል ምንም ዓይነት
ዝግጅት ማድረግ ባለመቻሉ በህብረተሰቡ ንብረትና ህይወት ላይ ጉዳት ሲደርስ ይታያል።
የቃጠለው መነሻ በመተመለከተ እስካሁን ድረስ የተገለጸ ነገር ባይኖርም የእስረኞች መኝታ ቤትና የምግብ ማብሰያ
ቤት ተጣብቆ መሰራቱ ሊሆን እንደሚችል ታዛቢዎች ያስረዳሉ።
በህግ እስረኞቹ ላይ እንዲህ አይነት አደጋ ሲደርስ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም ። የአደጋው መደጋገም በስልጣን
ላይ ያለው መንግስት በህግ እስረኞች ላይ ያለውን መጥፎ አያያዝ ያመለክታል ። በአንድ ክፍል ውስጥ የሚታሰሩ እስረኞች ቁጥር ከልክ
በላይ በመሆኑና በእስር ቤቶቹ አጠቃላይ ሁኔታ ክትትልና ቁጥጥር ስለማይደረግ በመላው አገሪቱ የሚገኙ እስር ቤቶች ህንጻ በእርጅና
ሲደረመስ ፤ በእሳት ቃጠሎና በሌሎች አጋጣሚዎች በሚከስት ድንገተኛ አደጋ የእስረኞችን ህይወት ያልፋል።
ባሳለፍነው ህዳር ወር 2005 ዓ/ም በዓ/ግራት ከተማ የሚገኝ አንድ እስር ቤት ተደርምሶ በውስጡ ከነበሩት
እስረኞች መካከል 27 ሲሞቱ በርካታ መቁሰላቸውን የሚታወስ ነው ።