በፓዊ ወረዳ በቀጠና አንድ የመንደር ቁጥር 3,4,5,6 እና 26 ኗሪዎች ቦታው ለስኳር ልማት ተፈልጓል
በሚል ምክንያት ከህዳር 2005 ዓ/ም ጀምሮ ቅድመ ዝግጅት ሳይደረግና ኗሪውን ሳያማክሩ የፌደራል ፖሊስ በአከባቢው በማሰማራት ህዝቡን
በሃይል ከቀየው እንዲነሳ እየተደረገ ነው።
ይህ በእንዲህ እያለ በአዊ ዞን ጃዊንና ፓዊን የሚያገናኝ የበለስ ወንዝ ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ከታህሳስ
10,2005 ዓ/ም ጀምሮ በአከባቢው የትራንስፖርት አገልግሎት ስለተቋረጠ ህዝቡ በችግር ላይ ይገኛል።
የሁለቱ ወረዳ ኗሪዎች ከታህሳስ 20,2005 ዓ/ም ጀምሮ ለሚመለከታቸው የሁለቱ ወረዳዎች ባለስልጣናት ችግራቸውን
ቢያቀርቡም ያገኙት ምላሽ የለም።