Thursday, February 14, 2013

ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የተበደሩትን ገንዘብ መመለስ ያልቻሉ በአዊ ዞን ፤ የጃዊ ወረዳ ኗሪዎች ከ3 የካቲት 2005 ዓ/ም ጀምሮ ንብረታቸን በተቋሙ ተወርሶ በመሸጥ ላይ መሆኑ ቷውቋል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በአማራ ህዝብ ስም የሚነግደው አ.ብ.ቅ.ተ ለህዝብ ተቆርቋሪ መስሎ በመቅረብ ህዝቡን ብድር እንዲወስድ ካደረገ ብሁዋላ ከገቢው በላይ ከፍተኛ ግብር በመጫንና ማዳበርያ በውድ ዋጋ የግድ እንዲገዛ በማድረግ ህዝቡን ማደህየታቸውን እንዳይበቃ የወሰደውን ብድር ተሎ እንዲመልስ ጫና በማድረግ የነበረውን ንብረት ሸጦ እንዲከፍል እያስገደዱት ነው፣
ይህ በእንዲህ እያለ በምእራብ ጎጃም ዞን ፤ በብር ሸሎቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ አከባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ ደን በማውደም ለግል ጥቅማቸው ለማዋል የአከባቢው የመስተዳድር አካላት ያደረጉት ሙከራ ተከትሎ በአከባቢው የህዝብ ተቋውሞ መቀስቀሱን ቷውቋል፣
በዚሁ ዞን በፖለቲካዊ አመለካከታቸው ምክንያት የውሸት ምስክርና የፈጠራ ክስ ተይዘው በፍኖተ ሰላም ከተማ በሚገኝ አንድ እስር ቤት ውስጥ እግራቸውና እጃቸው በሰንሰለት ተጠፍሮ በጨለማ ውስጥ በስቃይ ላይ የሚገኙ በርካታ የህሊን እስረኞች እንዳሉ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣