Thursday, February 14, 2013

በአድዋ ከተማ ከሚገኘው የቅድስተማሪያም ቴክኒክና ሞያ ትምህርት ቤት የተመረቁ ተማሪዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት የስራ እድል ተነፈገን ይላሉ፣




ከሞያና ቴክኒክ ት/ቤቶችና ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያየ ሞያ የሚመረቁ ተማሪዎች የህወሓት አባላት ባለመሆናቸው ብቻ በመንግስት መ/ቤቶች የስራ እድል ሲነፈጋቸው በአንጻሩ የድርጅቱ አባላት በቀላሉ ስራ እንዲያገኙ ይደረጋል ሲሉ አድልዎ ደርሶብናል የሚሉ ተማሪዎች ይናገራሉ፣
የኢህአደግ መንግስት በሚከተለው ብልሹ አሰራር ምክንያት የኢህአደግ አባል መሆን ከዜግነት በላይ እየታየ የድርጅቱ አባል የሆነ ተጠቃሚ ሲሆን አብዛኛው አባልነቱን ያልተቀበሉ ደግሞ የዜግነት መብቱ ሲጣስ ይታያል ፣በእንዲህ ዓይነቱ በአድልዎ የተሞላ አሰራር የተማረሩ በርካታ ተማሪዎች እስከ መቸ ተምረን እንዳልተማርን እንሆናለን ሁሉንም ዜጋ በእኩል የሚመለከት ስርዓት እንዲመጣ የድርሻችን ማበርከት አለብን በማለት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ገለጸዋል፣