Sunday, February 17, 2013

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የተደረገውን ተቃውሞ አነሳስተዋል በሚል የታሰሩ አስር ተማሪዎች በአድዋና በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ በሚገኙ እስር ቤቶች በእስር ላይ መሆናቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት ከታሰሩት ተማርዎች መካከል ሓጎስ አስመላሽ ፤ ትርሓስ ፍስሃየና ዮናስ መሓሪ የሚገኙባቸው ሲሆን በእስር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች በሙሉ ሳይፈቱና ያቀረብቱን ጥያቄ ምላሽ እስካላገኘ ድረስ መቃወማቸውን እንደማያቆሙ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ገልጸዋል ፣
ከፌደራል ፖሊስ በተቶኮሰባቸው ጥይት የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ተማሪዎች አወል መሓመድ ከብሄረ ትግራይና አንጀሎ እንኩዮ ከብሄረ ጋምቤላ መሆናቸውን ለማወቅ ተችለዋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ የካቲት 3,2005 ዓ/ም በሽዎች የሚቆጠሩ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢህአደግ ስርዓት ‘ጅሃዳዊ ሃረካት’ በሚል ርእስ በቴሌቪዥን ያስተላለፈውን የሃሰት ድራማ በመቃወም በጅማ ከተማ ተቃውማቸውን ገልጸዋል ፣
የጸረ-ህዝቡ ስርዓት አገልጋይ የሆነው የፌደራል ፖሊስ በተማሪዎቹ ላይ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅቶ ቢጠባበቅም ተማሪዎቹ ተቃውማቸውን በሰላማዊ መንገድ አሰምተው ወደ ግቢያቸው በመመለሳቸው ምክንያት የፌደራል ፖሊስ ፍላግት ሳይሳካ መቅረቱን ቷውቋል፣