በደረስን ዘገባ መሰረት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ መልካም አስተዳደር ፤አንድነትና መከባበር እንዳለ በማስመሰልና
የኢትዮጵያ ህዝብን ለማታለል ተብሎ በሰራዊቱ ስም እየተከበረ ያለው የይስሙላ በዓል በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኘ የሽረ እንዳስላሰ
ከተማ ኗሪዎች ተቃውሞ አንድ ማሳያ ነው፣ የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ባለመውጣቱ ምክንያት የከተማዋ ከንቲባ ፍስሓ ውበት
ንግግር ሳያደርግ በሃፍረት ወደ ጽ/ቤቱ መመለሱን ለማወቅ ተችለዋል ፣
የከተማዋ የመከላከያ ሰራዊት ቀንን ምክንያት በማድረግ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጣ በስርዓቱ ካድሬዎች የተሰጠውን
ትእዛዝ ያልተቀበለበት ዋና ምክንያት የኢህአዴግ መንግስት የህዝብን መሰረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ ስላልቻለና የምርጫ ካርድ ያልያዘ
ሰውም ከአከባቢው መልቀቅና ከሃገሪቱም መውጣት አለበት በማለት የህዝቡን የዜግነት መብት በካድሪዎች እየተጣሰ ባለበት ሁኔታ ማንኛውንም
በስርዓቱ የሚወጡ መመሪያዎችን ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ ኣይደንም ሲሉ የከተማዋ ኗሪዎች ይገልጻሉ፣
በተመሳሳይ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማና አከባቢዋ የሚገኙ የህወሓት-ኢህአደግ ካድሬዎች የምርጫ ካርድ ያልያዘ
ሰው ስኳር ፤ ዘይት የመሳሰሉ ሌሎች መሰረታዊ የፎጆታ ሽቀጦችን እንዳያገኝ መመርያ ማውረዳቸውን ቷውቋል ፣
ይህ በእንዲህ
እያለ የካቲት 11 ምክንያት በማድረግ ህዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ የሚል መመሪያ የካቲት 4,2005 ዓ/ም በህወሓት ካድሬዎች ቢወርድም
ህዝቡ ግን በዓሉ ልጆቻችን መስዋእትነት የከፈሉለትን ክቡር ዓላማና የተውሉንን አደራ የምናስታውስበትና የምናድስበት ክቡር በዓል
ቢሆንም ህወሓት የሰማእቶቻችንን አደራ ዋጋ በማሳጣት አራክሶታል የህወሓት አመራሮች በሰማእታት ስም ሲነግዱና ሲንደላቀቁ አብዛኛው
ህዝብ ግን በከባድ ችግር ላይ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት የሰማእቶቻችንን አደራ የረገጡ ጥቂት የህወሓት ካድሪዎች በዓሉን በማስመልከት
የመናገርም ሆነ ህዝቡንም ገንዘብ እንዲያዋጣ የመጠይቅ የሞራል ብቃት የላቸውም ሰማእቶቻችን ሁሌም ቢሆን በልቦናችን ውስጥ ስለሆኑ
ማንም አስመሳይና ከሃዲ እንዲነግረን አንጠብቅም በማለት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ገልጸዋል፣