Thursday, March 28, 2013

በያዝነው ሳምንት የተካሄደው 11ኛ የህወሓት ጉባኤና የአመራር ምርጫ መላውን የትግራይ ህዝብ እያነጋገረ ያለ አሳዛኝ ጉዳይ ሆኗል፣



ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎበት ከመጋቢት 8-11,2005 ዓ/ም ድረስ ለአራት ቀናት የተካሄደው ጉባኤ ውጤቱ ለመላው የትግራይ ህዝብና ለአብዛኛው የድርጅቱ አባላትን ያሳዘነ ሲሆን በተለይም አቅም እንደሌለው በሰፊው የሚነገርለት አባይ ወልዱ የህወሓት ሊቀመንበር ሆኖ ዳግም መመረጡ በድርጅቱ ውስጥ አቅም ያለው ሰው አለመኖሩን የሚያሳይና በዛው ልክም የድርጅቱ አቅም በጣም ማሽቆልቆሉን የሚያመለት ነው ፣ እየተነገረለት ያለው መተካካትም የእውነት መተካካት ሳይሆን ለይምሰል የሚደረግ የሰዎች መቀያየር ነው በማለት ህዝቡን በሰፊው እያነጋገረ ያለ ጉዳይ መሆኑ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
በተለይም በፍላጎታቸው ከድርጅቱ መሰናበታቸውን እየተነገረን ያለ የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ ስናይ ሆን ብለው ተግባራቸውን አውቀው አስቀድመው ከተጠያቂነት ለማምለጥና በድርጅቱ ውስጥ ከተከሰተው መሰነጣጠቅም እራስን ለማራቅ የሚደረግ ከስጋት የመነጨ ተግባር እንጂ እውነት ስልጣን ይብቃን ብለው ለመጭው ትውልድ ለማስረከብ ተነሳሽነቱ ኖሯቸው አይደለም የሚል ነገር በሰፊው ይነገራል፣
በመጨረሻም በጉኣቤው የተሳተፉ አንዳንድ ወገኖች ስለጉባኤው ተጠይቀው እንደተናገሩት ከሆነ ጉባኤው የሚያሳዝንና ተስፋ የሚያስቆርጥ እንደነበር በህወሓት ታሪክ ውስጥ ከተደረጉት ጉባኤዎች እጅግ የወረደና የድርጅቱንም ህልውና ያበቃለት መሆኑን ያመላከተ አጋጣሚ ነበር በማለት ሁሉም ነገር በተንኮል የተሰራ ተሳታፊውንም በአንድ ለአምስት አደረጃጀት በመከፋፈል ያካሄዱት የምርጫ ሂደት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነበር ሲሉ ይደመጣሉ፣
ከድርጅቱ በፍላጎታቸው ተሰናበቱ የተባሉ ዘጠኛ የድርጅቱ አባላት፣---
1-         ስዩም መስፍን
2-         አርከበ ዕቑባይ
3-         ዘርአይ አስገዶም
4-         ብርሃነ ገ/ክርስቶስ
5-         ንጉሰ ገብረ
6-         ሕሸ ለማ
7-         መሰረት ገ/ማሪያም
8-         ደስታ በርሀ
9-         መንግስተአብ ገ/ኪዳን  ናቸው፣