Thursday, March 28, 2013

በሽረ-እንዳስላሰ ወረዳ የፖሊስ ጽ/ቤት የተንሰራፋውን ሙስና መፍትሄ እንዲደረግበት የጠየቁ የፖሊስ አባላት ማስፈራርያና ቅጣት እንደደረሰባቸው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን በሽረ-እንዳስላሰ ወረዳ የሚገኙ የፖሊስ አዛዦችና አመራሮች እንቅስቃሴ ህግንና ስርዓትን የተከተለ ሳይሆን ስልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም በጉቦና አድልዎ የማይገብቸውን ሃብት ሲያካብቱ ይታያሉ ፣ አሰራሩን በግልጽ በሚቃወሙ የፖሊስ አባላት ላይም ፈጣን እርምጃ እንደሚወሰዱባቸው ቷውቋል፣
ሙሶኞችን በማጋለጣቸው ምክንያት እርምጃ ከተወሰደባቸው የፖሊስ አባላት መካከል ብርሃነ ሽሻይ የተባለ የምርመራ ስራ ሲሰራ የነበረ አንድ የፖሊስ አባል ይገኝበታል፣ በፖሊስ አባሉ ላይ እርምጃ የተወሰደው አባሉ በወረዳዋ በፖሊስ አባላት የሚሰሩ ስራዎች ሁሉ በጉቦና አድልዎ መሆኑን ጠቅሶ አሰራሩ የህዝብን ተአማኒነትን የሚያሳጣ ፤ እድገትንና ልማትንም የሚያሰናክል በመሆኑ ሙስናን ለማስወገድ ጠንካራ እርምጃ መወሰድ አለበት ሲል ሃሳብ በማቅረቡ መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል፣
የፖሊስ አባሉ በሙስና ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ባቀረበው ሃሳብ ቅር የተሰኙ ሙሰኛ የፖሊስ አዛዦች የፖሊስ አባሉ የፖሊስ አባሉ ጎቦና አድልዎ ተንሰራፍቷል ብሎ በመናገሩ የፖሊስ ስም አጥፍታል ፤ በህዝብ ዘንድ የነበረንን ተአማኒነት እንድናጣ በማድረግ ሆን ብሎ የፖሊስ ስራን ለማደናቀፍ የተነሳ በማስመሰልና በማጥላላት ከስራ እንዲባረር መወሰናቸው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣