Thursday, March 28, 2013

የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ዜጎችን በማስፈራራት ገንዘብ እንደሚዘርፉ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የክ/ሃገር አውቶብስ ተራ ህጋዊ የፖሊስ አባላት መስለው በመቅረብ አንድን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪን ማንነቱን በመጠየቅና ይዞት የነበረውን ሞባይልንና ላፕ ቶፕን በመቀማት ገንዘብ ካልሰጣቸው እንደሚያስሩት በማስፈራራት ገንዘብ እንደተቀበሉት ለማወቅ ተችለዋል፣
ተማሪው በህግ የተፈለገበትን ምክንያት ለፖሊስ አባላቱ በጠየቀበት ወቅት እስኪጣራ ድረስ በእስር ቤት ትቆያለህ ቶሎ መለቀቅ ከፈለግክ ገንዘብ ክፈል እንዳሉትና እሱም ትምህርቱን ላለሟቋረጥና ህይወቱንም ለማትረፍ ሲል ለስንቅ ቤተሰቡ የሰጡትን ገንዘብ ከፍሎ መገላገል መምረጡን ተማሪው ተናግሯል፣
በስርዓቱ የፖሊስ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ እየተፈጸመ ያለው ህጋዊ በመምሰል የዜጎችን ገንዘብ የመዝረፍ ተግባር በመላው የሃገሪቱ ከተሞች ጭምር እየተለመደ የመጣ ህገወጥ ተግባር መሆኑ የሚታወስ ነው ፣