Monday, March 4, 2013

የአማራንና የትግራይ ክልልን የሚያገናኘው በመታደሰና አስፋልት በመሆን ላይ ካለው ዋና የመኪና መንገድ በሽረ እንዳስላሰ ከተማ ክልል ውስጥ የሚያልፈው መንገድ ብቻ ስድስት ወር ሳይሞላው ዳግም ከጥቅም ውጭ መሆኑ ቷውቋል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት የመንገድ ስራው ደህና እየተሰራ መጥቶ ክረምት 2004 ዓ/ም ሽረ ከተማ ሲደርስ በቀናት ልዩነት ውስጥ መፈራረስ በመጀመሩ በወቅቱ ከፈተኛ የህዝብ ተቋውሞ ተነስቶ ኮንትራቱን የወሰደው የቻይና ተቋራጭ የከተማዋን ህዝብ ተቋውሞ ምክንያት ስራውን መቀጠል ስላልቻለ የመንገድ ግምባታ ስራ ለግዜው የተጓጐለ ሲሆን ጉዳዩ ክልልን አልፎ እስከ ፌደራል ድረስ ደርሶ የከተማዋ ህዝብ 6 ሚልዮን ብር እንዲያዋጣና የተበላሸው የአስፋልት ንጣፍ ተነስቶ በአዲስ መልክ እንዲሰራ ቢደረግም ተሰራ የተባለው በከተማው ክልል ውስጥ የሚያልፈው መንገድ በ 6 ወራት ውስጥ ዳግም ከጥቅም ውጭ ሆኖ በአሁኑ ግዜ አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል፣
የህወሓት የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ቴዎድሮ ሓጎስ ሃምሌ 2004 ከአመሪካ ሬድዮ የትግሪኛ አግልግሎት መፍረስ ስለጀመረው የአስፋልት ንጣፍንና የከተማዋን ህዝብ ተቋውሞን በማስመልክት ለቀረበላቸው ጥያቄ ችግር መኖሩ አምነው ተቀብለው ፤ ብቃት ያለው ተቋራጭ በክልሉ ያለመኖር ለተከሰተው ችግር በዋናነት እንደምክንያት ለማስቀመጥ መኩረዋል፣
ነግር ግን ኮንትራት የወሰደው የቻይና ተቋራጭ በብቃቱ ተወዳድሮና በህጋዊ ጨረታ አሸንፎ መሆኑ በመግስት ሚድያዎች በወቅቱ ተገልጻል፣ ኮንትራት የወሰደውም ሁለቱንም ክልሎች የሚያገናኘው ዋና መንገድ በአጠቅላይ ለመስራት እንጂ በከተማዋ የሚያልፈውን መንገድ ብቻ በመነጠል አልነበረም በመሆኑም በከተማዋ ክልል ውስጥ የሚያልፈው መንገድ ብቻ ከአንዴም ሁሌቴ መበላሸት በተቋራጩ ብቃት ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ ሳይሆን ከበላይ ስራውን በመምራት ላይ ያሉ የመንግስት ባለስልጣናት በተለይም የክልሉ ባለስልጣናት ችግር ነው ሲሉ የከተማዋ ናሪዎች ይናገራሉ፣
የከተማዋ ኗሪ ለስራው የተጠየቀውን ሁሉ አማልቶ እያለ በከተማዋ ክልል የሚያልፈው መንገድ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ ባለመሰራቱና ከህዝብ የተዋጣው ገንዘብም በመባከኑ ምክንያት የተቀሰቀሰውን የህዝብ ቁጣ ከወዲሁ ለማለዘብ ሲባል በክልሉ የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች የከተማዋን ኗሪ ህዝብ በተከታታይ ስብሰባ ጠምደውታል፣
ፕሮጀችቱን ተረክቦ ሁለቱንም ክልሎች የሚያገናኘውን ዋና መንገድ በመስራት ላይ የነበረው  የቻይናው ተቋራጭም በወቅቱ ስራውን እንዲያቆም ከከተማዋ ህዝብ የቀረበለትን ጥያቄ ተከትሎ በከተማዋ የሚያልፈው መንገድ ጥራት የጎደሎው ቢሆንም በውላችን መሰረት እየሰራን ነው ሲል መናገሩንና በከተማዋ በተቀሰቀሰው ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞም ጉዳዩ እስከ ፌደራል ድረስ ደርሶ መስከረም 2005 ዓ/ም የተበላሸው የአስፋልት ንጣፉ ተነስቶ ዳግም እንዲሰራ መደረጉን የሚታወስ ነው፣