Wednesday, March 6, 2013

በጅማ ከተማ በሚገኙ የኦህዴድ ካድሬዎች የተካሄደ ስብሰባ ያለ ውጤት መበተኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣

በደረሰን ዘገባ መሰረት በጅማ ከተማ በሁሉም ቀበሌዎች የሚገኙ የኦህዴድ አባላትን ያሳተፈ ‘ዘመቻ መለስ ለእምርታ’ በሚል መሪ ቃል ለካቲት 24 ና 25/2005 ዓ/ም በግቤ አዳራሽ የተካሄደው ስብሰባ የህወሓትን የበላይነት ያንጸባርቃል በማለት ተሰብሳቢዎቹ እንዳልተቀበሉት ቷውቋል፣
በተጨማሪ ህወሓት-ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ ከግፍና ጭቆና በማላቀቅ ሰላምና ዴሞክራሲ በሃገሪቱ እንዲሰፍንና ልማት እንዲረጋገጥ ባካሄደው የትጥቅ ትግል የተከፈለው መስዋእትነት በታሪክ የላቀ ክብር ይሰጠዋል በሚለው ላይ የህወሓትን ታላቅነትን በማንጸባረቅ የሌሎችን አባል ድርጅቶች ሚና አሳንሶ የሚያሳይ ነው ሲሉ ካድሬዎቹ መቋወማቸውን ለማወቅ ተችለዋል፣
ተሰብሳቢዎቹ አጀንዳው ህወሓት በትጥቅ ትግሉ የነብረውን ሚና የሚያጎላ እንጂ የክልላችንና የሃገሪቱ አስተዋጽኦን አይወክልም በማለት ስብሰባውን መቃወማቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣