Wednesday, April 3, 2013

የመቐለ ከተማ ህዝብ ለአባይ ግድብ ቦንድ እዲገዛ እየተገደደ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል፣



የከተማዋ ኗሪ በዚህ ዓመት መግብያ ቀደም ሲል ገዝተናል አይበቃም ወይ ብሎ በሚጠይቅበት ግዜ ፕሮጆክቱ 80 ቢልዮን ወጪ የሚጠይቅ ነው ፣ እስካሁን ድረስ በሃገር ደረጃ የተገኘው 20 ቢልዮን ብቻ ነው ፣ ገንዘባችሁ የትም አይሄድም ባንክ ውስጥ እንዳለ ቁጠሩት በማለት በተለይም በዚህ ሳምንት የግድቡ መጀመር ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ “የመለስን አደራ እናስክብር” በሚል ህዝቡን ለሁለተኛ ግዜ ቦንድ እንዲገዛ እያደረጉት መሆኑ ቷውቋል፣
እኛ ህዝቡን በማስተባበር በራሳችን ወጪ ግድቡን ለመስራት ስለፈለግን እንጂ ገንዘብ ከሌሎች አገሮች ተበድረን ማሰራት እንችላለን በማለት ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ጫና ያደርጋሉ፣
ካድሬዎቹ ህዝቡን በመቀስቀስ በነበሩበት ግዜ አንድ የከተማዋ ኗሪ በመሰረታዊ የፍጆታ ሽቀጦች እንደ ስኳር ፤ ዘይትና ሌሎች አቅርቦት እጥረት ህዝቡ ተቸግሮ እያለ በያዝነው ዓመት ለሁለተኛ ግዜ ቦንድ እንድን ገዛ ማስገደዳቸው ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው በማለት በስርዓቱ ያለውን ቅሬታ መግለጹን የደርሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣