በደረሰን ዘገባ መሰረት የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ሲገለገልበት የነበረ አንድ ሞተር በመጥፋቱ ምክንያት አምስት
ሰራተኞች ያለ ምንም ተጨባጭ ማስረጃና የፍርድ ቤት ትእዛዝ በፖሊስ ተይዘው አሶሳ ከተማ በሚገኝ አንድ እስር ቤት ታስረው ይገኛሉ፣
ይህ በእንዲህ እያለ በስራ ተሰማርተው ከነበሩት GM ገልባጭ መኪናዎች መካከል መጋቢት 14/2005 ዓ/ም
በሁለት ተሽከርካሪዎች መካከል በተከሰተው ግጭት ምክንያት ከአከባቢው ከፍተኛ ሙቀት ጋር ተደማምሮ ሁለቱም ተሽከርካሪዎች በእሳት
ተያይዘው ከስራ ውጭ መሆናቸውንና ሁኔታው የአከባቢው ሃላፊዎች ለሰው ህይወትም ሆነ ለንብረት የሚሰጡት ቱክረት ዝቅተኛ መሆኑን የሚያመለክት
ነው ሲሉ በአከባቢው የሚገኙ ባለሞያዎች ይናገራሉ፣