የከተማዋ ኗሪዎች በከተማዋ ባለው የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት ምክንያት ሩቅ ተጉዘው ከሚያገኙት
ጥራት የጎደለው የጉድጓድ ውሃ ለመጠቀም በመገደዳቸው ኗሪው ባጠቃላይ በተለይም ሴቶችና ህጻናት ለተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታዎች መዳረጋቸውን
ቷውቋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በከተማዋ የሞባይል ኔት ወርክ አግልግሎት ችግር በመከሰቱ ምክንያት ኔጋዴዎች ፤ የመንግስት
ሰራተኞችና ባጠቃላይ ኗሪው ህዝብ እለታዊ ስራውን በአግባቡ ለመስራት መቸገሩን ለማወቅ ተችለዋል፣
የሞባይል ኔት ወርክ መቆራረጥ ችግር መንግስት ከህወሓት ጉባኤ ጋር በተያያዘ በአከባቢው ህዝብ ላይ ባለው
ስጋት ምክንያት ሆን ብሎ ዘግቶት ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ በሰፊው ሲነገር ይደመጣል፣
የስርዓቱ
ካድሬዎች መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የስልጣን መተካካት በማድረግ ወጣቱ ሃላፊነት የሚረከብበት ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑ ቢነገርም
የከተማዋ ህዝብ ግን አባሉን እንደ ማይቀበለው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣