በሰ/ምዕራብ ትግራይ የደደቢትና የዓዲ-መሐመዳይ የመብራት ፣ የውሃና የፍትህ አገልግሎት በአግባቡ ያለማግኘት
ችግር መፍትሄ እንዲደረግለት በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ አቅርበው ችግሩ ስላልተቃለለ ኗሪዎቹ ያማርራሉ።
ኗሪዎቹ እንደሚሉት ከታች ተመድበው ህዝቡን በአግባቡ ማገልገል ያልቻሉ የመንግስት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ
ከሃላፊነታቸው መነሳት አለባቸው በማለት ለሚመለከተው አካል ሃሳብ ቢያቀርቡም ግለሰቦቹ በዘረፉት የህዝብ ገንዘብና ከበላይ የመንግስት
ባለስልጣናት ጋር ባላቸው ቁርኝት በመተማመን በህዝቡ ላይ በደል መፈጸም ቀጥለውበታል በማለት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ይገልጻሉ።
የአከባቢው
ኗሪዎች ለችግሮቻቸው መፍትሄ ፍለጋ ወደ ዞን መስተዳድር ቢሄዱም መልስ እኪሰጣችሁ ድረስ ጉዳዩን በተመለከተ ምንም ነገር ወደ ህዝብ
እንዳይቀርብ የሚል ማስፈራሪያና ዛቻ እንሰተሰጣቸው ቷውቃል።