Saturday, May 11, 2013

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ ወታደሮች የዓመት እርፍት ፈቃድ እንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ቅር መሰኘታቸውን ቷውቋል።

በክልሉ ተሰማርተው የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊት አባላት የዓመት ዕረፍት እንደዚሁም ቤተሰብን ለመጠየቅ ፈቃድ እንዲሰጣቸው በሚጠይቁበት ግዜ ፈቃድ እንደማያገኙና በመሰረቱም ፈቃድ አይሰጥም የሚል ዝግ የሆነ መልስ እንደሚሰጣቸው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በመከላከያ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ማንኛውም ወታደር የዓመት እረፍት የማግኘት መብት እንዳለው የተቀመጠ ቢሆንም ህገ ደምቡ ተግባራዊ ስለማይሆንና ወታደሮቹ ፈቃድ አግኝተው ቤተሰባቸውን ለመጠየቅ ያላቸውን ህጋዊ መብት ስለሚከለከሉ ወታደሩ ሃገሩን እየተወ እንዲኮበልልና ወደ ስደት እንዲያመራ ይገደዳል።
በዚህ ምክንያት የሰራዊቱ አባላትና እርስ በእርሳቸው ይሁን ከአዝዦቻቸው ጋር ስምምነት ሰለሌላቸው ወታደራዊ ግዳጅን ሊወጡ አይችሉም። በተገኘው ስብሰባ ሁሉ ጥያቅያቸው መልስ እንዲያገኝ በተደጋጋሚ በማቅረብና የአመራሮቻቸውን ስሜት በመንካት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይፈጽሙ እያደረጉ መሆኑ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።