በደረሰን ዘገባ መሰረት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፣ በጉማ ወረዳ ፣ በማንኩሽ ንኡስ ወረዳ እየተገነባ ያለው
የህዳሴው ግድብ በተመለከተ በኢህአደግ ካድሬዎች የሚናፈሰው ወሬ ማስተጋባት መደበኛ ስራቸው አድርገው የወሰዱ የስርዓቱ ሚድያ ተብየዎች
በየግዜው የሚያቀርቡት ዘገባ ውሽትና በመሬት ላይ የሌለ ህዝቡን ለማደናገር ተብሎ የሚደረግ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
በስራው ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች እንደሚሉት የፕሮጀችቱን እንቅስቃሴ በተመለከተ የመንግስት ሚድያዎች እንደሚያቀርቡት
ሳይሆን በመጀመሪያ ደረጃ እንደሚገኝ ፣ በዚሁ አያያዝ ከቀጠለ በአምስት ዓመታት ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደማይችል ፣ ፕሮጀክቱ በተያዘለት
የግዜ ሰሌዳ ተጠናቅቆ ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ ከተፈለገ በፕሮጀክቱ ተሰማርተው በስራ ላይ ያሉና እስካሁን ድረስ ደመወዝ ባለመከፈላቸው
የሚያማርሩ ሰራተኞችን መብት ጠበቅ ይገባ ነበር።
በዚህም ምክንያት ሰራተኛው ደስተኛ ሆኖ እንደማይሰራና ጎብኝዎች በሚመጡበት ግዜ ብቻ ለማስመሰል የሚንቀሳቀስ
የተሰላቸ ሆኗል።
የፋሲካን
በዓል ምክንያት በማድረግ ከሚያዝያ 23, 2005 ዓ/ም ጀምረው ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱ በርካታ የግድቡ ሰራተኞች ወደ ስራቸው ስላልተመለሱ
አብዛኛው የግድብ ስራ መቆሙ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።