በኦሮሚያ ክልል ፣ በቦሮና ዞን ፣ መንግስት የቅድስት አርሴማን ቤተክርስትያን ያለችበትን አከባቢ ለእርሻ
ልማት ስለሚፈለግ ለቤተ ክርስትያና ሌላ ተለዋጭ ቦታ ተሰጥቶ ካለችበት ቦታ እንድትነሳ የተላለፈውን ውሳኔ ለእርሻ ልማት የሚሆን
ነጻ መሬት እያለ በልማት ስም ቤተክርስትያንን ማፍረስ አይገባም በማለት የአከባቢው ህዝብ ተቃውመውን በቁጣ በመግለጽ ይገኛል።
ውሳኔው የተሰጠው በዞኑ አስተዳደር አቶ ኡዱ ገመዳ ሲሆን እንዲህ ዓይነቱን ሃላፊነት የጎደለው ተግባር በስልጣን
ላይ ያለው መንግስት በተደጋጋሚ ለዘመናት ተጠብቀው የቆዩትን የእምነት ተቋማትን አብያተ ክርስትያናት ፣ ገዳማትና መስጊዶች እንደዚሁም
የኢትዮጵያ ህዝብ ማንነት መገለጫ በሆኑት ታሪካዊ ቦታዎች ላይ እየወሰደው ያለ አውዳሚ እርምጃ በመቃወም በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር
ውጭ የሚገኙ ዜጎች ተቃውማቸውን በተለያዩ ግዜ ሲገልጹ መቆየታቸው የሚታወስ ነው ።